Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - Amhaarse vertaling - Mohammed Sadiq

Pagina nummer:close

external-link copy
141 : 4

ٱلَّذِينَ يَتَرَبَّصُونَ بِكُمۡ فَإِن كَانَ لَكُمۡ فَتۡحٞ مِّنَ ٱللَّهِ قَالُوٓاْ أَلَمۡ نَكُن مَّعَكُمۡ وَإِن كَانَ لِلۡكَٰفِرِينَ نَصِيبٞ قَالُوٓاْ أَلَمۡ نَسۡتَحۡوِذۡ عَلَيۡكُمۡ وَنَمۡنَعۡكُم مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۚ فَٱللَّهُ يَحۡكُمُ بَيۡنَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَلَن يَجۡعَلَ ٱللَّهُ لِلۡكَٰفِرِينَ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ سَبِيلًا

እነዚያ በእናንተ (የጊዜን መዘዋወር) የሚጠባበቁ ናቸው፡፡ ለእናንተም ከአላህ የኾነ አሸናፊነት ቢኖራችሁ «ከእናንተ ጋር አልነበርንምን» ይላሉ፡፡ ለከሓዲዎችም ዕድል ቢኖር «(ከአሁን በፊት) በእናንተ ላይ አልተሾምንምን (እና አልተውናችሁምን) ከምእምናንም (አደጋ) አልከለከልናችሁምን» ይላሉ፡፡ አላህም በትንሣኤ ቀን በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡ አላህም ለከሓዲዎች በምእምናን ላይ መንገድን በፍጹም አያደርግም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
142 : 4

إِنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ يُخَٰدِعُونَ ٱللَّهَ وَهُوَ خَٰدِعُهُمۡ وَإِذَا قَامُوٓاْ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ قَامُواْ كُسَالَىٰ يُرَآءُونَ ٱلنَّاسَ وَلَا يَذۡكُرُونَ ٱللَّهَ إِلَّا قَلِيلٗا

መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ (ይቀጣቸዋል)፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
143 : 4

مُّذَبۡذَبِينَ بَيۡنَ ذَٰلِكَ لَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ وَلَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلٗا

በዚህ መካከል ወላዋዮች ኾነው (ያሳያሉ)፡፡ ወደ እነዚህም ወደ እነዚያም አይደሉም፡፡ አላህም ያሳሳተውን ሰው ለእርሱ (የቅንነት) መንገድን በፍፁም አታገኝለትም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
144 : 4

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجۡعَلُواْ لِلَّهِ عَلَيۡكُمۡ سُلۡطَٰنٗا مُّبِينًا

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ፤ ለአላህ በናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን info
التفاسير:

external-link copy
145 : 4

إِنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ فِي ٱلدَّرۡكِ ٱلۡأَسۡفَلِ مِنَ ٱلنَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمۡ نَصِيرًا

መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነሱም ረዳትን አታገኝላቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
146 : 4

إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ وَأَصۡلَحُواْ وَٱعۡتَصَمُواْ بِٱللَّهِ وَأَخۡلَصُواْ دِينَهُمۡ لِلَّهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ مَعَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۖ وَسَوۡفَ يُؤۡتِ ٱللَّهُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ أَجۡرًا عَظِيمٗا

እነዚያ የተመለሱ (ሥራቸውን) ያሳመሩም፤ በአላህም የተጠበቁ፤ ሃይማኖታቸውንም ለአላህ ፍጹም ያደረጉ ሲቀሩ፡፡ እነዚያስ ከምእምናን ጋር ናቸው፡፡ ለምእምናንም አላህ ታላቅን ምንዳ በእርግጥ ይሰጣል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
147 : 4

مَّا يَفۡعَلُ ٱللَّهُ بِعَذَابِكُمۡ إِن شَكَرۡتُمۡ وَءَامَنتُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ شَاكِرًا عَلِيمٗا

ብታመሰግኑና ብታምኑ አላህ እናንተን በመቅጣት ምን ያደርጋል አላህም ወረታን መላሽ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير: