Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - Amhaarse vertaling - Mohammed Sadiq

Pagina nummer:close

external-link copy
87 : 4

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ لَيَجۡمَعَنَّكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِۗ وَمَنۡ أَصۡدَقُ مِنَ ٱللَّهِ حَدِيثٗا

አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው info
التفاسير:

external-link copy
88 : 4

۞ فَمَا لَكُمۡ فِي ٱلۡمُنَٰفِقِينَ فِئَتَيۡنِ وَٱللَّهُ أَرۡكَسَهُم بِمَا كَسَبُوٓاْۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَهۡدُواْ مَنۡ أَضَلَّ ٱللَّهُۖ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلٗا

በመናፍቃንም (ነገር) አላህ በሥራዎቻቸው ወደ ክህደት የመለሳቸው ሲኾኑ ሁለት ክፍሎች የኾናችሁት ለናንተ ምን አላችሁ አላህ ያጠመመውን ሰው ልታቀኑ ታስባላችሁን አላህ ያሳሳተውን ሰው ለእርሱ መንገድን ፈጽሞ አታገኝለትም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
89 : 4

وَدُّواْ لَوۡ تَكۡفُرُونَ كَمَا كَفَرُواْ فَتَكُونُونَ سَوَآءٗۖ فَلَا تَتَّخِذُواْ مِنۡهُمۡ أَوۡلِيَآءَ حَتَّىٰ يُهَاجِرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَخُذُوهُمۡ وَٱقۡتُلُوهُمۡ حَيۡثُ وَجَدتُّمُوهُمۡۖ وَلَا تَتَّخِذُواْ مِنۡهُمۡ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرًا

(እነርሱ) እንደ ካዱ ብትክዱና እኩል ብትኾኑ ተመኙ! በአላህም ሃይማኖት እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ወዳጆችን አትያዙ፡፡ (ከእምነት) ቢያፈገፍጉም ያዙዋቸው፤ (ማርኩዋቸው)፡፡ ባገኛችሁበትም ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ ከእነሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
90 : 4

إِلَّا ٱلَّذِينَ يَصِلُونَ إِلَىٰ قَوۡمِۭ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُم مِّيثَٰقٌ أَوۡ جَآءُوكُمۡ حَصِرَتۡ صُدُورُهُمۡ أَن يُقَٰتِلُوكُمۡ أَوۡ يُقَٰتِلُواْ قَوۡمَهُمۡۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَسَلَّطَهُمۡ عَلَيۡكُمۡ فَلَقَٰتَلُوكُمۡۚ فَإِنِ ٱعۡتَزَلُوكُمۡ فَلَمۡ يُقَٰتِلُوكُمۡ وَأَلۡقَوۡاْ إِلَيۡكُمُ ٱلسَّلَمَ فَمَا جَعَلَ ٱللَّهُ لَكُمۡ عَلَيۡهِمۡ سَبِيلٗا

እነዚያ በእናንተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ወዳላቸው ሕዝቦች የሚጠጉና ወይም እናንተን ለመጋደል ወይም ወገኖቻቸውን ለመጋደል ልቦቻቸው የተጨነቁ ኾነው የመጧዋችሁ ሲቀሩ፤ (እነዚያንስ አትጋደሉዋቸው)፡፡ አላህም በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ኀይል በሰጣቸውና በተጋደሉዋችሁ ነበር፡፡ ቢተዋችሁና ባይጋደሉዋችሁም ወደ እናንተም እርቅን ቢያቀርቡ አላህ ለእናንተ በነሱ ላይ (የመጋደል) መንገድን አላደረገም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
91 : 4

سَتَجِدُونَ ءَاخَرِينَ يُرِيدُونَ أَن يَأۡمَنُوكُمۡ وَيَأۡمَنُواْ قَوۡمَهُمۡ كُلَّ مَا رُدُّوٓاْ إِلَى ٱلۡفِتۡنَةِ أُرۡكِسُواْ فِيهَاۚ فَإِن لَّمۡ يَعۡتَزِلُوكُمۡ وَيُلۡقُوٓاْ إِلَيۡكُمُ ٱلسَّلَمَ وَيَكُفُّوٓاْ أَيۡدِيَهُمۡ فَخُذُوهُمۡ وَٱقۡتُلُوهُمۡ حَيۡثُ ثَقِفۡتُمُوهُمۡۚ وَأُوْلَٰٓئِكُمۡ جَعَلۡنَا لَكُمۡ عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٗا مُّبِينٗا

ሌሎች ከእናንተ ለመዳን ከወገኖቻቸውም ለመዳን የሚፈልጉን ታገኛላችሁ፡፡ ወደ እውከት እንዲመለሱ በተደረጉ ቁጥር በርሷ ውስጥ ይመለሳሉ፡፡ ባይተውዋችሁና እርቅንም ባያቀርቡላችሁ፣ እጆቻቸውንም ባይሰበስቡ፣ ባገኛችኋቸው ስፍራ ማርኩዋቸው፡፡ ግደሉዋቸውም፡፡ እነዚያንም ለእናንተ በነሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን አድርገናል፡፡ info
التفاسير: