ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
82 : 21

وَمِنَ ٱلشَّيَٰطِينِ مَن يَغُوصُونَ لَهُۥ وَيَعۡمَلُونَ عَمَلٗا دُونَ ذَٰلِكَۖ وَكُنَّا لَهُمۡ حَٰفِظِينَ

82.ከሰይጣናትም ለእርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያ ሌላ ያለን ስራ የሚሰሩን ገራንለት፤ ለእነርሱም ተጠባባቂዎች ነበርን:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 21

۞ وَأَيُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَسَّنِيَ ٱلضُّرُّ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ

83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ:: አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ።» ሲል በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። info
التفاسير:

external-link copy
84 : 21

فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ فَكَشَفۡنَا مَا بِهِۦ مِن ضُرّٖۖ وَءَاتَيۡنَٰهُ أَهۡلَهُۥ وَمِثۡلَهُم مَّعَهُمۡ رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِنَا وَذِكۡرَىٰ لِلۡعَٰبِدِينَ

84. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን:: ቤተሰቦቹንም ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው:: info
التفاسير:

external-link copy
85 : 21

وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِدۡرِيسَ وَذَا ٱلۡكِفۡلِۖ كُلّٞ مِّنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

85. ኢስማዒልንም፤ ኢድሪስንም፤ ዙልኪፍልንም፤ አስታውስ:: ሁሉም ከታጋሾች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 21

وَأَدۡخَلۡنَٰهُمۡ فِي رَحۡمَتِنَآۖ إِنَّهُم مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

86. በችሮታችንም ውስጥ አስገባናቸው:: እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና:: info
التفاسير:

external-link copy
87 : 21

وَذَا ٱلنُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَٰضِبٗا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقۡدِرَ عَلَيۡهِ فَنَادَىٰ فِي ٱلظُّلُمَٰتِ أَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبۡحَٰنَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ:: ዓሳም ዋጠው:: በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ «ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ:: እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ።» በማለት ተጣራ። info
التفاسير:

external-link copy
88 : 21

فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَنَجَّيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡغَمِّۚ وَكَذَٰلِكَ نُـۨجِي ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

88. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ከጭንቅም አዳነው:: ልክ እንደዚሁም ምዕምናንን እናድናለን:: info
التفاسير:

external-link copy
89 : 21

وَزَكَرِيَّآ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرۡنِي فَرۡدٗا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡوَٰرِثِينَ

89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ:: አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ።» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ አስታውስ። info
التفاسير:

external-link copy
90 : 21

فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ يَحۡيَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥٓۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَيَدۡعُونَنَا رَغَبٗا وَرَهَبٗاۖ وَكَانُواْ لَنَا خَٰشِعِينَ

90. ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው:: ለእርሱም የህያን ሰጠነው:: ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት:: እነርሱ በበጎ ስራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ:: ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ:: info
التفاسير: