ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
73 : 21

وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَئِمَّةٗ يَهۡدُونَ بِأَمۡرِنَا وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِمۡ فِعۡلَ ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰةِۖ وَكَانُواْ لَنَا عَٰبِدِينَ

73. በትእዛዛችንም ወደ በጎ ስራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው:: ወደነሱም መልካም ስራዎችን መስራትን፤ ሶላትንም መስገድን ዘካንም መስጠትን አወረድን:: ለእኛም ተገዢዎች ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
74 : 21

وَلُوطًا ءَاتَيۡنَٰهُ حُكۡمٗا وَعِلۡمٗا وَنَجَّيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡقَرۡيَةِ ٱلَّتِي كَانَت تَّعۡمَلُ ٱلۡخَبَٰٓئِثَۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمَ سَوۡءٖ فَٰسِقِينَ

74. ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው:: ከዚያችም መጥፎ ስራዎችን ትሰራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው:: እነርሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 21

وَأَدۡخَلۡنَٰهُ فِي رَحۡمَتِنَآۖ إِنَّهُۥ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

75. በችሮታችንም ውስጥ አስገባነው:: እርሱ ከመልካሞች አንዱ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 21

وَنُوحًا إِذۡ نَادَىٰ مِن قَبۡلُ فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ فَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ

76.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኑሕንም ከዚያ በፊት ጌታውን በጠራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፤ እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን:: info
التفاسير:

external-link copy
77 : 21

وَنَصَرۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمَ سَوۡءٖ فَأَغۡرَقۡنَٰهُمۡ أَجۡمَعِينَ

77.ከእነዚያም በታዓምራቶቻችን ከአስተባበሉት ህዝቦች ተንኮል ጠበቅነው:: እነርሱ ክፉ ህዝቦች አመጸኞች ነበሩና ሁሉንም አሰመጥናቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
78 : 21

وَدَاوُۥدَ وَسُلَيۡمَٰنَ إِذۡ يَحۡكُمَانِ فِي ٱلۡحَرۡثِ إِذۡ نَفَشَتۡ فِيهِ غَنَمُ ٱلۡقَوۡمِ وَكُنَّا لِحُكۡمِهِمۡ شَٰهِدِينَ

78.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ ! ) ዳውድንና ሱለይማንንም በአዝመራው ነገር በሚፈርዱ ጊዜ የህዝቦቸ ፍየሎች ሌሊት በእርሱ ውስጥ በተሰማሩ ጊዜ አስታውስ:: ፍርዳቸውንም አዋቂዎች ነበርን:: info
التفاسير:

external-link copy
79 : 21

فَفَهَّمۡنَٰهَا سُلَيۡمَٰنَۚ وَكُلًّا ءَاتَيۡنَا حُكۡمٗا وَعِلۡمٗاۚ وَسَخَّرۡنَا مَعَ دَاوُۥدَ ٱلۡجِبَالَ يُسَبِّحۡنَ وَٱلطَّيۡرَۚ وَكُنَّا فَٰعِلِينَ

79. ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው:: ለሁሉም ጥበብንና እውቀትን ሰጠን:: ተራራዎችን ከዳውድ ጋር የሚያወድሱ ሲሆን ገራን፤ አእዋፍንም እንደዚሁ ገራን ሰሪዎችም ነበርን። info
التفاسير:

external-link copy
80 : 21

وَعَلَّمۡنَٰهُ صَنۡعَةَ لَبُوسٖ لَّكُمۡ لِتُحۡصِنَكُم مِّنۢ بَأۡسِكُمۡۖ فَهَلۡ أَنتُمۡ شَٰكِرُونَ

80.የብረት ልብስንም ስራ ለእናንተ ከጦራችሁ ትጠብቃችሁ ዘንድ አስተማርነው:: እናንተ አመስጋኞች ናችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
81 : 21

وَلِسُلَيۡمَٰنَ ٱلرِّيحَ عَاصِفَةٗ تَجۡرِي بِأَمۡرِهِۦٓ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَاۚ وَكُنَّا بِكُلِّ شَيۡءٍ عَٰلِمِينَ

81. ለሱለይማንም ነፋስን በኃይል የምትነፍስ በትእዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (ወደ ሻም) የምትነፍስ ስትሆን (ገራንለት) በነገሩ ሁሉም አዋቂዎች ነበርን:: info
التفاسير: