ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
36 : 21

وَإِذَا رَءَاكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِي يَذۡكُرُ ءَالِهَتَكُمۡ وَهُم بِذِكۡرِ ٱلرَّحۡمَٰنِ هُمۡ كَٰفِرُونَ

36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች ባዩህ ጊዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይዙህም። እነርሱ በአር-ረህማን መወሳት እነርሱ ከሓዲያን ሲሆኑ: «ያ አማልክቶቻችሁን በክፉ የሚያነሳቸው ይህ ነውን?» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 21

خُلِقَ ٱلۡإِنسَٰنُ مِنۡ عَجَلٖۚ سَأُوْرِيكُمۡ ءَايَٰتِي فَلَا تَسۡتَعۡجِلُونِ

37. ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ:: ታዓምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 21

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

38. «እውነተኞች ከሆናቸሁ ይህ ቀጠሮም መቼ ነው?» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 21

لَوۡ يَعۡلَمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ حِينَ لَا يَكُفُّونَ عَن وُجُوهِهِمُ ٱلنَّارَ وَلَا عَن ظُهُورِهِمۡ وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ

39.እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ከፊቶቻቸውና ከጀርቦቻቸው ላይ እሳትን የማይከለክሉበትን እነርሱም የማይረዳዱበትን ጊዜ ቢያውቁ ኖሮ ይህንን አይሉም ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 21

بَلۡ تَأۡتِيهِم بَغۡتَةٗ فَتَبۡهَتُهُمۡ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ رَدَّهَا وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ

40. ይልቁንም ሰዓቲቱ በድንገት ትመጣቸዋለች:: ታስደነግጣቸዋለችም:: መመለሷንም አይችሉም:: እነርሱም የሚቆይላቸው አይደሉም። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 21

وَلَقَدِ ٱسۡتُهۡزِئَ بِرُسُلٖ مِّن قَبۡلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُواْ مِنۡهُم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም የነበሩት መልዕክተኞች በእርግጥ ተቀለደባቸው፤ በእነዚያ ከእነርሱ ይቀልዱ በነበሩት ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ሰፈረባቸው። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 21

قُلۡ مَن يَكۡلَؤُكُم بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ مِنَ ٱلرَّحۡمَٰنِۚ بَلۡ هُمۡ عَن ذِكۡرِ رَبِّهِم مُّعۡرِضُونَ

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከአር-ረህማን ቅጣት በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው?» በላቸው:: በእውነቱ እነርሱ ከጌታቸው ግሠጼ ከቁርኣን ዘንጊዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 21

أَمۡ لَهُمۡ ءَالِهَةٞ تَمۡنَعُهُم مِّن دُونِنَاۚ لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَ أَنفُسِهِمۡ وَلَا هُم مِّنَّا يُصۡحَبُونَ

43.ለእነርሱ ከእኛ ሌላ የምትከላከልላቸው አማልዕክት አለቻቸውን? ነፍሶቻቸውን መርዳትን አይችሉም:: እነርሱም (ከሓዲያኑ) ከእኛ አይጠብቁም። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 21

بَلۡ مَتَّعۡنَا هَٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمۡ حَتَّىٰ طَالَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡعُمُرُۗ أَفَلَا يَرَوۡنَ أَنَّا نَأۡتِي ٱلۡأَرۡضَ نَنقُصُهَا مِنۡ أَطۡرَافِهَآۚ أَفَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ

44.በእውነትም እነዚህንና አባቶቻቸውን በእነርሱ ላይ ዕድሜ እስከ ረዘመባቸው ድረስ አጣቀምናቸው:: ተታለሉም። እኛ ምድርን ከጫፎቿ የምናጎድላት ሆነን ስንመጣባት አያዩምን? እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን? info
التفاسير: