ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
58 : 21

فَجَعَلَهُمۡ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرٗا لَّهُمۡ لَعَلَّهُمۡ إِلَيۡهِ يَرۡجِعُونَ

58. ዘወር ሲሉም ስብርብሮች አደረጋቸው:: ለእነርሱ የሆነ አንድ ትልቅ ጣዖት ብቻ ሲቀር :: ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ እርሱን ብቻ ተወው። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 21

قَالُواْ مَن فَعَلَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَآ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

59. «በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራ ማነው? እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
60 : 21

قَالُواْ سَمِعۡنَا فَتٗى يَذۡكُرُهُمۡ يُقَالُ لَهُۥٓ إِبۡرَٰهِيمُ

60. «ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (ወጣት) በመጥፎ ሲያነሳቸው ሰምተናል።» ተባባሉ። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 21

قَالُواْ فَأۡتُواْ بِهِۦ عَلَىٰٓ أَعۡيُنِ ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَشۡهَدُونَ

61. «ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎች ዓይን ፊት ላይ አምጡት።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
62 : 21

قَالُوٓاْ ءَأَنتَ فَعَلۡتَ هَٰذَا بِـَٔالِهَتِنَا يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ

62. «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሰራህ አንተ ነህን?» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
63 : 21

قَالَ بَلۡ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمۡ هَٰذَا فَسۡـَٔلُوهُمۡ إِن كَانُواْ يَنطِقُونَ

63. «አይደለም:: ይህ ትልቃቸው ሰራው፤ ይናገሩም እንደ ሆነ ጠይቋቸው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 21

فَرَجَعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ فَقَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ أَنتُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

64. ወደ ነፍሶቻቸዉም ተመለሱ: «እናንተ በመጠየቃችሁ በዳዮቹ እናንተው ናችሁ።» ተባባሉም። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 21

ثُمَّ نُكِسُواْ عَلَىٰ رُءُوسِهِمۡ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا هَٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ

65. ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡና «እነዚህ የሚናገሩ አለመሆናቸውን በእርግጥ አውቀሃል።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
66 : 21

قَالَ أَفَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَا يَضُرُّكُمۡ

66.ኢብራሂምም አላቸው: «ታዲያ ለእናንተ ብታመልኳቸው ምንም የማይጠቅማችሁንና ባታመልኳቸዉም በምንም ነገር የማይጎዳችሁን ጣዖታትን ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
67 : 21

أُفّٖ لَّكُمۡ وَلِمَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

67. «ኡፍ! ለእናንተም ሆነ ከአላህ ሌላ ለምትገዙት ጣዖታት። አታስተውሉምን?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
68 : 21

قَالُواْ حَرِّقُوهُ وَٱنصُرُوٓاْ ءَالِهَتَكُمۡ إِن كُنتُمۡ فَٰعِلِينَ

68. «ሰሪዎች (ተቆርቋሪዎች) እንደ ሆናችሁ ኢብራሂምን በእሳት አቃጥሉት አማልክቶቻችሁንም እርዱ።» አሉ:: (በእሳት ላይ ጣሉትም።) info
التفاسير:

external-link copy
69 : 21

قُلۡنَا يَٰنَارُ كُونِي بَرۡدٗا وَسَلَٰمًا عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ

69. «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛና ሰላም ሁኚ።» አልን። info
التفاسير:

external-link copy
70 : 21

وَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَخۡسَرِينَ

70. በእርሱም ተንኮልን አሰቡ። በጣም ከሳሪዎች አደረግናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
71 : 21

وَنَجَّيۡنَٰهُ وَلُوطًا إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَا لِلۡعَٰلَمِينَ

71. እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች በውስጡ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር በመውሰድ አዳንናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 21

وَوَهَبۡنَا لَهُۥٓ إِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ نَافِلَةٗۖ وَكُلّٗا جَعَلۡنَا صَٰلِحِينَ

72.ለእርሱም ኢስሐቅን ያዕቆብንም ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው:: ሁሉንም መልካሞች አደረግን:: info
التفاسير: