ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
54 : 18

وَلَقَدۡ صَرَّفۡنَا فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ لِلنَّاسِ مِن كُلِّ مَثَلٖۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ أَكۡثَرَ شَيۡءٖ جَدَلٗا

በዚህም ቁርኣን ውስጥ ከየምሳሌው ሁሉ ለሰዎች መላልሰን ገለጽን፡፡ ሰውም ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ክርክረ ብዙ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 18

وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤۡمِنُوٓاْ إِذۡ جَآءَهُمُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّهُمۡ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمۡ سُنَّةُ ٱلۡأَوَّلِينَ أَوۡ يَأۡتِيَهُمُ ٱلۡعَذَابُ قُبُلٗا

ሰዎችንም መምሪያ በመጣላቸው ጊዜ ከማመንና ጌታቸውንም ምሕረትን ከመለመን የመጀመሪዎቹ (ሕዝቦች) ልማድ (መጥፋት) ልትመጣባቸው ወይም ቅጣቱ በያይነቱ ሊመጣባቸው (መጠባበቅ) እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 18

وَمَا نُرۡسِلُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَۚ وَيُجَٰدِلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِٱلۡبَٰطِلِ لِيُدۡحِضُواْ بِهِ ٱلۡحَقَّۖ وَٱتَّخَذُوٓاْ ءَايَٰتِي وَمَآ أُنذِرُواْ هُزُوٗا

መልክተኞችንም አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች ኾነው እንጂ አንልክም፡፡ እነዚያ የካዱትም በውሸት እውነቱን በእሱ ሊያበላሹ ይከራከራሉ፡፡ አንቀጾቼንና በእርሱ የተስፈራሩበትንም ነገር ማላገጫ አድርገው ያዙ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 18

وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ فَأَعۡرَضَ عَنۡهَا وَنَسِيَ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُۚ إِنَّا جَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۖ وَإِن تَدۡعُهُمۡ إِلَى ٱلۡهُدَىٰ فَلَن يَهۡتَدُوٓاْ إِذًا أَبَدٗا

በጌታውም አንቀጾች ከተገሰጸና ከእርሷ ከዞረ እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር ከረሳ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እኛ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን በጆሮዎቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን፡፡ ወደ መመራትም ብትጠራቸው ያን ጊዜ ፈጽሞ አይምመሩም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 18

وَرَبُّكَ ٱلۡغَفُورُ ذُو ٱلرَّحۡمَةِۖ لَوۡ يُؤَاخِذُهُم بِمَا كَسَبُواْ لَعَجَّلَ لَهُمُ ٱلۡعَذَابَۚ بَل لَّهُم مَّوۡعِدٞ لَّن يَجِدُواْ مِن دُونِهِۦ مَوۡئِلٗا

ጌታህም በጣም መሃሪው የእዝነት ባለቤቱ ነው፡፡ በሠሩት ሥራ ቢይዛቸው ኖሮ ቅጣቱን ለእነሱ ባስቸኮለባቸው ነበር፡፡ ግን ለእነሱ ከእርሱ ሌላ መጠጊያን ፈጽሞ የማያገኙበት ቀጠሮ አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 18

وَتِلۡكَ ٱلۡقُرَىٰٓ أَهۡلَكۡنَٰهُمۡ لَمَّا ظَلَمُواْ وَجَعَلۡنَا لِمَهۡلِكِهِم مَّوۡعِدٗا

እነዚህ ከተሞችም (ነዋሪዎቿን) በበደሉ ጊዜ አጠፋናቸው፡፡ ለመጥፊያቸውም የተወሰነ ጊዜን አደረግን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
60 : 18

وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِفَتَىٰهُ لَآ أَبۡرَحُ حَتَّىٰٓ أَبۡلُغَ مَجۡمَعَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ أَوۡ أَمۡضِيَ حُقُبٗا

ሙሳም ለወጣቱ «የሁለቱን ባሕሮች መገናኛ እስከምደርስ ወይም ብዙን ጊዜ እስከምኼድ ድረስ (ከመጓዝ) አልወገድም» ያለውን ጊዜ (አስታውስ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
61 : 18

فَلَمَّا بَلَغَا مَجۡمَعَ بَيۡنِهِمَا نَسِيَا حُوتَهُمَا فَٱتَّخَذَ سَبِيلَهُۥ فِي ٱلۡبَحۡرِ سَرَبٗا

የሁለቱን መገናኛ በደረሱም ጊዜ ዐሣቸውን ረሱ፡፡ (ዐሣው) መንገዱንም በባህሩ ውስጥ ቀዳዳ አድርጎ ያዘ፡፡ info
التفاسير: