ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
35 : 18

وَدَخَلَ جَنَّتَهُۥ وَهُوَ ظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ قَالَ مَآ أَظُنُّ أَن تَبِيدَ هَٰذِهِۦٓ أَبَدٗا

እርሱም ነፍሱን በዳይ ኾኖ ወደ አትክልቱ ገባ፡፡ «ይህች ዘለዓለም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 18

وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّدِدتُّ إِلَىٰ رَبِّي لَأَجِدَنَّ خَيۡرٗا مِّنۡهَا مُنقَلَبٗا

«ሰዓቲቱንም ቋሚ (ኋኝ) ናት ብዬ አልጠረጥርም፡፡ (እንደምትለው) ወደ ጌታዬም ብመለስ ከእርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ» (አለው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 18

قَالَ لَهُۥ صَاحِبُهُۥ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَكَفَرۡتَ بِٱلَّذِي خَلَقَكَ مِن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ سَوَّىٰكَ رَجُلٗا

ጓደኛው (አማኙ) እርሱ ለእርሱ የሚመላለሰው ሲኾን «በዚያ ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከፈጠረህ፣ ከዚያም ሰው ባደረገህ (አምላክ) ካድክን» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 18

لَّٰكِنَّا۠ هُوَ ٱللَّهُ رَبِّي وَلَآ أُشۡرِكُ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا

«እኔ ግን እርሱ አላህ ጌታዬ ነው፤ (እላለሁ)፡፡ በጌታዬም አንድንም አላጋራም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 18

وَلَوۡلَآ إِذۡ دَخَلۡتَ جَنَّتَكَ قُلۡتَ مَا شَآءَ ٱللَّهُ لَا قُوَّةَ إِلَّا بِٱللَّهِۚ إِن تَرَنِ أَنَا۠ أَقَلَّ مِنكَ مَالٗا وَوَلَدٗا

«አትክልትህንም በገባህ ጊዜ አላህ የሻው ይኾናል፤ በአላህ ቢኾን እንጂ ኀይል የለም፤ አትልም ኖሯልን እኔን በገንዘብም በልጅም ካንተ በጣም ያነስኩ ሆኜ ብታየኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 18

فَعَسَىٰ رَبِّيٓ أَن يُؤۡتِيَنِ خَيۡرٗا مِّن جَنَّتِكَ وَيُرۡسِلَ عَلَيۡهَا حُسۡبَانٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَتُصۡبِحَ صَعِيدٗا زَلَقًا

«ጌታዬ ከአትክልትህ የበለጠን ሊሰጠኝ በርሷም (በአትክልትህ) ላይ ከሰማይ መብረቆችን ሊልክባትና የምታንዳልጥ ምልጥ ምድር ልትኾን ይቻላል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 18

أَوۡ يُصۡبِحَ مَآؤُهَا غَوۡرٗا فَلَن تَسۡتَطِيعَ لَهُۥ طَلَبٗا

ወይም ውሃው ሠራጊ ሊኾን (ይችላል)፡፡ ያን ጊዜ ለርሱ መፈለግን ፈጽሞ አትችልም» (አለው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 18

وَأُحِيطَ بِثَمَرِهِۦ فَأَصۡبَحَ يُقَلِّبُ كَفَّيۡهِ عَلَىٰ مَآ أَنفَقَ فِيهَا وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُشۡرِكۡ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا

በሀብቱም ተከበበ (ተጠፋ)፡፡ እርሷ በዳሶቿ ላይ የወደቀች ኾና በእርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ (እየተጸጸተ) መዳፎቹን የሚያገላብጥና «ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድም ባላጋራሁ» የሚል ኾነ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 18

وَلَمۡ تَكُن لَّهُۥ فِئَةٞ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مُنتَصِرًا

ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ጭፍሮች አልነበሩትም፡፡ ተረጂም አልነበረም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 18

هُنَالِكَ ٱلۡوَلَٰيَةُ لِلَّهِ ٱلۡحَقِّۚ هُوَ خَيۡرٞ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ عُقۡبٗا

እዚያ ዘንድ (በትንሣኤ ቀን) ስልጣኑ እውነተኛ ለኾነው አላህ ብቻ ነው፡፡ እርሱ በመመንዳት የበለጠ ፍጻሜንም በማሳመር የበለጠ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
45 : 18

وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا كَمَآءٍ أَنزَلۡنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخۡتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلۡأَرۡضِ فَأَصۡبَحَ هَشِيمٗا تَذۡرُوهُ ٱلرِّيَٰحُۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ مُّقۡتَدِرًا

ለእነሱም የቅርቢቱን ሕይወት ምሳሌ አውሳላቸው፡፡ (እርሷ) ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር በቃይ እንደ ተቀላቀለበት (ከተዋበ በኋላ ደርቆ) ነፋሶችም የሚያበኑት ደቃቅ እንደ ኾነ ብጤ ናት፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ info
التفاسير: