ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
46 : 18

ٱلۡمَالُ وَٱلۡبَنُونَ زِينَةُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَٱلۡبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّٰلِحَٰتُ خَيۡرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ أَمَلٗا

ገንዘብና ወንዶች ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው፡፡ መልካሞቹም ቀሪዎች (ሥራዎች) እጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው፡፡ በተስፋም በላጭ ናቸው፡፤ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 18

وَيَوۡمَ نُسَيِّرُ ٱلۡجِبَالَ وَتَرَى ٱلۡأَرۡضَ بَارِزَةٗ وَحَشَرۡنَٰهُمۡ فَلَمۡ نُغَادِرۡ مِنۡهُمۡ أَحَدٗا

ተራራዎችንም የምናስኼድበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ምድርንም ግልጽ ኾና ታያታለህ፡፡ እንሰበስባቸዋለንም፡፡ ከእነሱም አንድንም አንተውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
48 : 18

وَعُرِضُواْ عَلَىٰ رَبِّكَ صَفّٗا لَّقَدۡ جِئۡتُمُونَا كَمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةِۭۚ بَلۡ زَعَمۡتُمۡ أَلَّن نَّجۡعَلَ لَكُم مَّوۡعِدٗا

የተሰለፉም ኾነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ፡፡ (ይባላሉም) «በመጀመሪያ ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ (ራቁታችሁን) በእርግጥ መጣችሁን በእውነቱ ለእናንተ (ለመቀስቀሻ) ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
49 : 18

وَوُضِعَ ٱلۡكِتَٰبُ فَتَرَى ٱلۡمُجۡرِمِينَ مُشۡفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَٰوَيۡلَتَنَا مَالِ هَٰذَا ٱلۡكِتَٰبِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةٗ وَلَا كَبِيرَةً إِلَّآ أَحۡصَىٰهَاۚ وَوَجَدُواْ مَا عَمِلُواْ حَاضِرٗاۗ وَلَا يَظۡلِمُ رَبُّكَ أَحَدٗا

(ለሰው ሁሉ) መጽሐፉም ይቀርባል፡፡ ወዲያውም ከሓዲዎችን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ «ዋ ጥፋታችን! ለዚህ መጽሐፍ (ከሥራ) ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢኾን እንጂ የማይተወው ምን አለው» ይላሉም፡፡ የሰሩትንም ነገር ሁሉ ቀራቢ ኾኖ ያገኙታል፡፡ ጌታህም አንድንም አይበድልም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
50 : 18

وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ كَانَ مِنَ ٱلۡجِنِّ فَفَسَقَ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِۦٓۗ أَفَتَتَّخِذُونَهُۥ وَذُرِّيَّتَهُۥٓ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِي وَهُمۡ لَكُمۡ عَدُوُّۢۚ بِئۡسَ لِلظَّٰلِمِينَ بَدَلٗا

ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ከጋኔን (ጎሳ) ነበር፡፡ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ፡፡ እርሱንና ዘሮቹን እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ሲኾኑ ከእኔ ላይ ረዳቶች አድርጋችሁ ትይዛላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
51 : 18

۞ مَّآ أَشۡهَدتُّهُمۡ خَلۡقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَا خَلۡقَ أَنفُسِهِمۡ وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ ٱلۡمُضِلِّينَ عَضُدٗا

የሰማያትንና የምድርን አፈጣጠር አላሳየኋቸውም፡፡ የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር (እንደዚሁ)፡፡ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
52 : 18

وَيَوۡمَ يَقُولُ نَادُواْ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُمۡ فَدَعَوۡهُمۡ فَلَمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَهُمۡ وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُم مَّوۡبِقٗا

«እነዚያንም (አምላክ) የምትሏቸውን ተጋሪዎቼን ጥሩ» የሚልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ይጠሯቸዋልም ግን አይመልሱላቸውም፡፡ በመካከላቸውም መጥፊያን ስፍራ (ገሀነምን) አደረግን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
53 : 18

وَرَءَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ ٱلنَّارَ فَظَنُّوٓاْ أَنَّهُم مُّوَاقِعُوهَا وَلَمۡ يَجِدُواْ عَنۡهَا مَصۡرِفٗا

ከሓዲዎችም እሳትን ያያሉ፡፡ እነርሱም በውስጧ ወዳቂዎች መኾናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ከእርሷም መሸሻን አያገኙም፡፡ info
التفاسير: