ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
75 : 18

۞ قَالَ أَلَمۡ أَقُل لَّكَ إِنَّكَ لَن تَسۡتَطِيعَ مَعِيَ صَبۡرٗا

«አንተ ከኔ ጋር ትእግሥትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩህምን?» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
76 : 18

قَالَ إِن سَأَلۡتُكَ عَن شَيۡءِۭ بَعۡدَهَا فَلَا تُصَٰحِبۡنِيۖ قَدۡ بَلَغۡتَ مِن لَّدُنِّي عُذۡرٗا

«ከርሷ (ከአሁኒቱ ጊዜ) በኋላ ከምንም ነገር ብጠይቅህ አትጎዳኘኝ፡፡ ከእኔ የይቅርታን መጨረሻ በእርግጥ ደርሰሃል» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
77 : 18

فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰٓ إِذَآ أَتَيَآ أَهۡلَ قَرۡيَةٍ ٱسۡتَطۡعَمَآ أَهۡلَهَا فَأَبَوۡاْ أَن يُضَيِّفُوهُمَا فَوَجَدَا فِيهَا جِدَارٗا يُرِيدُ أَن يَنقَضَّ فَأَقَامَهُۥۖ قَالَ لَوۡ شِئۡتَ لَتَّخَذۡتَ عَلَيۡهِ أَجۡرٗا

ኼዱም፡፡ ወደ አንዲት ከተማ ሰዎች በመጡም ጊዜ ነዋሪዎቿን ምግብን ጠየቁ፡፡ ከማስተናገዳቸውም እምቢ አሉ፡፡ በእርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን ግድግዳ አገኙ፡፡ (ኸደር) አቆመውም፡፡ (ሙሳም) «በሻህ ኖሮ በእርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
78 : 18

قَالَ هَٰذَا فِرَاقُ بَيۡنِي وَبَيۡنِكَۚ سَأُنَبِّئُكَ بِتَأۡوِيلِ مَا لَمۡ تَسۡتَطِع عَّلَيۡهِ صَبۡرًا

(ኸደር) አለ «ይህ በእኔና በአንተ መካከል መለያያ ነው፡፡ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልክበትን ፍች እነግርሃለሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
79 : 18

أَمَّا ٱلسَّفِينَةُ فَكَانَتۡ لِمَسَٰكِينَ يَعۡمَلُونَ فِي ٱلۡبَحۡرِ فَأَرَدتُّ أَنۡ أَعِيبَهَا وَكَانَ وَرَآءَهُم مَّلِكٞ يَأۡخُذُ كُلَّ سَفِينَةٍ غَصۡبٗا

«መርከቢቱማ በባሕር ለሚሠሩ ምስኪኖች ነበረች፡፡ ከኋላቸውም መርከብን ሁሉ በቅሚያ የሚይዝ ንጉሥ ነበረና፤ (እንዳይቀማቸው) ላነውራት ፈለግኩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
80 : 18

وَأَمَّا ٱلۡغُلَٰمُ فَكَانَ أَبَوَاهُ مُؤۡمِنَيۡنِ فَخَشِينَآ أَن يُرۡهِقَهُمَا طُغۡيَٰنٗا وَكُفۡرٗا

«ወጣቱም ልጅማ ወላጆቹ ምእመናን ነበሩ፡፡ (ቢያድግ) ትእቢትንና ክህደትንም የሚያስገድዳቸው መኾኑን ፈራን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
81 : 18

فَأَرَدۡنَآ أَن يُبۡدِلَهُمَا رَبُّهُمَا خَيۡرٗا مِّنۡهُ زَكَوٰةٗ وَأَقۡرَبَ رُحۡمٗا

«ጌታቸውም በንጹሕነት ከእርሱ በላጭን በእዝነትም ከእርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
82 : 18

وَأَمَّا ٱلۡجِدَارُ فَكَانَ لِغُلَٰمَيۡنِ يَتِيمَيۡنِ فِي ٱلۡمَدِينَةِ وَكَانَ تَحۡتَهُۥ كَنزٞ لَّهُمَا وَكَانَ أَبُوهُمَا صَٰلِحٗا فَأَرَادَ رَبُّكَ أَن يَبۡلُغَآ أَشُدَّهُمَا وَيَسۡتَخۡرِجَا كَنزَهُمَا رَحۡمَةٗ مِّن رَّبِّكَۚ وَمَا فَعَلۡتُهُۥ عَنۡ أَمۡرِيۚ ذَٰلِكَ تَأۡوِيلُ مَا لَمۡ تَسۡطِع عَّلَيۡهِ صَبۡرٗا

«ግድግዳውማ በከተማይቱ ውስጥ የነበሩ የሁለት የቲሞች ወጣቶች ነበር፡፡ በሥሩም ለእነርሱ የኾነ (የተቀበረ) ድልብ ነበረ፡፡ አባታቸውም መልካም ሰው ነበር፡፡ ጌታህም ለአካለ መጠን እንዲደርሱና ከጌታህ ችሮታ ድልባቸውን እንዲያወጡ ፈለገ፡፡ በፈቃዴም አልሠራሁትም፡፡ ይህ በእርሱ ላይ መታገስን ያልቻልከው ነገር ፍች ነው» (አለው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
83 : 18

وَيَسۡـَٔلُونَكَ عَن ذِي ٱلۡقَرۡنَيۡنِۖ قُلۡ سَأَتۡلُواْ عَلَيۡكُم مِّنۡهُ ذِكۡرًا

ከዙልቀርነይንም ይጠይቁሃል፡፡ «በእናንተ ላይ ከእርሱ ወሬን አነባለሁ፤» በላቸው፡፡ info
التفاسير: