ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
63 : 11

قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي مِنۡهُ رَحۡمَةٗ فَمَن يَنصُرُنِي مِنَ ٱللَّهِ إِنۡ عَصَيۡتُهُۥۖ فَمَا تَزِيدُونَنِي غَيۡرَ تَخۡسِيرٖ

«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም የሆነን ችሮታ (ነቢይነት) ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማነው ከማሳሳትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
64 : 11

وَيَٰقَوۡمِ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمۡ ءَايَةٗۖ فَذَرُوهَا تَأۡكُلۡ فِيٓ أَرۡضِ ٱللَّهِۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابٞ قَرِيبٞ

ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት፡፡ ተውዋትም፡፡ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» (አላቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
65 : 11

فَعَقَرُوهَا فَقَالَ تَمَتَّعُواْ فِي دَارِكُمۡ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٖۖ ذَٰلِكَ وَعۡدٌ غَيۡرُ مَكۡذُوبٖ

ወግተው (ገደሏትም)፡፡ (ሷሊህ) «በአገራችሁም ሶስትን ቀናት (ብቻ) ተጠቀሙ፡፡ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
66 : 11

فَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا صَٰلِحٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَمِنۡ خِزۡيِ يَوۡمِئِذٍۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡعَزِيزُ

ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳን፡፡ ከዚያም ቀን ውርደት (አዳንናቸው)፡፡ ጌታህ እርሱ ብርቱው አሸናፊው ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
67 : 11

وَأَخَذَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلصَّيۡحَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دِيَٰرِهِمۡ جَٰثِمِينَ

እነዚያንም የበደሉትን ጩኸት ያዛቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ የተንበረከኩ ሆነው ሞተው አነጉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
68 : 11

كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَآۗ أَلَآ إِنَّ ثَمُودَاْ كَفَرُواْ رَبَّهُمۡۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّثَمُودَ

በእሷ ውስጥ እንዳልኖሩባት ሆኑ፡፡ ንቁ! ሰሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ፡፡ ንቁ! ለሰሙዶች (ከአላህ እዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
69 : 11

وَلَقَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُنَآ إِبۡرَٰهِيمَ بِٱلۡبُشۡرَىٰ قَالُواْ سَلَٰمٗاۖ قَالَ سَلَٰمٞۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَآءَ بِعِجۡلٍ حَنِيذٖ

መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
70 : 11

فَلَمَّا رَءَآ أَيۡدِيَهُمۡ لَا تَصِلُ إِلَيۡهِ نَكِرَهُمۡ وَأَوۡجَسَ مِنۡهُمۡ خِيفَةٗۚ قَالُواْ لَا تَخَفۡ إِنَّآ أُرۡسِلۡنَآ إِلَىٰ قَوۡمِ لُوطٖ

እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
71 : 11

وَٱمۡرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٞ فَضَحِكَتۡ فَبَشَّرۡنَٰهَا بِإِسۡحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسۡحَٰقَ يَعۡقُوبَ

ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡ info
التفاسير: