ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
54 : 11

إِن نَّقُولُ إِلَّا ٱعۡتَرَىٰكَ بَعۡضُ ءَالِهَتِنَا بِسُوٓءٖۗ قَالَ إِنِّيٓ أُشۡهِدُ ٱللَّهَ وَٱشۡهَدُوٓاْ أَنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ

«ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር (በዕብደት) ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም» (አሉ)፡፡ «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ፡፡ ከምታጋሩትም እኔ ንጹሕ መሆኔን መስክሩ» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 11

مِن دُونِهِۦۖ فَكِيدُونِي جَمِيعٗا ثُمَّ لَا تُنظِرُونِ

ከእርሱ ሌላ (አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ)፡፡ ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ፤ ከዚያም አታቆዩኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 11

إِنِّي تَوَكَّلۡتُ عَلَى ٱللَّهِ رَبِّي وَرَبِّكُمۚ مَّا مِن دَآبَّةٍ إِلَّا هُوَ ءَاخِذُۢ بِنَاصِيَتِهَآۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

«እኔ በጌታዬና በጌታችሁ በአላህ ላይ ተጠጋሁ፡፡ በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ፡፡ ጌታዬ (ቃሉም ሥራውም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው» (አላቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 11

فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُم مَّآ أُرۡسِلۡتُ بِهِۦٓ إِلَيۡكُمۡۚ وَيَسۡتَخۡلِفُ رَبِّي قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ وَلَا تَضُرُّونَهُۥ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ حَفِيظٞ

«ብትዞሩም በእርሱ ወደእናንተ የተላክሁበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ፡፡ ጌታዬ ከእናንተ ሌላ ሕዝብም ይተካል ምንም አትጎዱትምም፡፡ ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና» (አላቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 11

وَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا هُودٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَنَجَّيۡنَٰهُم مِّنۡ عَذَابٍ غَلِيظٖ

ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን፡፡ ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 11

وَتِلۡكَ عَادٞۖ جَحَدُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ وَعَصَوۡاْ رُسُلَهُۥ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَمۡرَ كُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٖ

ይህች (ነገድ) ዓድ ናት፡፡ በጌታቸው ታምራት ካዱ፡፡ መልክተኞቹንም አመጹ፤ የኃያል ሞገደኛን ሁሉ ትዕዛዝም ተከተሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
60 : 11

وَأُتۡبِعُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا لَعۡنَةٗ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ أَلَآ إِنَّ عَادٗا كَفَرُواْ رَبَّهُمۡۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّعَادٖ قَوۡمِ هُودٖ

በዚህች በቅርቢቱ ዓለምም እርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ፡፡ በትንሣኤም ቀን (እንደዚሁ)፡፡ ንቁ! ዓዶች ጌታቸውን ካዱ፡፡ ንቁ! የሁድ ሕዝቦች ለሆኑት ዓዶች (ከእዝነት) መራቅ ይገባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
61 : 11

۞ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمۡ صَٰلِحٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَٱسۡتَعۡمَرَكُمۡ فِيهَا فَٱسۡتَغۡفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٞ مُّجِيبٞ

ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
62 : 11

قَالُواْ يَٰصَٰلِحُ قَدۡ كُنتَ فِينَا مَرۡجُوّٗا قَبۡلَ هَٰذَآۖ أَتَنۡهَىٰنَآ أَن نَّعۡبُدَ مَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِي شَكّٖ مِّمَّا تَدۡعُونَآ إِلَيۡهِ مُرِيبٖ

«ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ፡፡ አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን» አሉ፡፡ info
التفاسير: