ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
46 : 11

قَالَ يَٰنُوحُ إِنَّهُۥ لَيۡسَ مِنۡ أَهۡلِكَۖ إِنَّهُۥ عَمَلٌ غَيۡرُ صَٰلِحٖۖ فَلَا تَسۡـَٔلۡنِ مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٌۖ إِنِّيٓ أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ

(አላህም) «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 11

قَالَ رَبِّ إِنِّيٓ أَعُوذُ بِكَ أَنۡ أَسۡـَٔلَكَ مَا لَيۡسَ لِي بِهِۦ عِلۡمٞۖ وَإِلَّا تَغۡفِرۡ لِي وَتَرۡحَمۡنِيٓ أَكُن مِّنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

«ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
48 : 11

قِيلَ يَٰنُوحُ ٱهۡبِطۡ بِسَلَٰمٖ مِّنَّا وَبَرَكَٰتٍ عَلَيۡكَ وَعَلَىٰٓ أُمَمٖ مِّمَّن مَّعَكَۚ وَأُمَمٞ سَنُمَتِّعُهُمۡ ثُمَّ يَمَسُّهُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٞ

«ኑሕ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ፡፡ (ከእነሱው ዘሮች የሆኑ) ሕዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን፡፡ ከዚያም ከኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይነካቸዋል» ተባለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
49 : 11

تِلۡكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡغَيۡبِ نُوحِيهَآ إِلَيۡكَۖ مَا كُنتَ تَعۡلَمُهَآ أَنتَ وَلَا قَوۡمُكَ مِن قَبۡلِ هَٰذَاۖ فَٱصۡبِرۡۖ إِنَّ ٱلۡعَٰقِبَةَ لِلۡمُتَّقِينَ

ይህቺ ከሩቁ ወሬዎች ናት፡፡ ወደ አንተ እናወርዳታለን፡፡ አንተም ሕዝቦችህም ከዚህ በፊት የምታውቋት አልነበራችሁም፡፡ ታገስም፤ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ናትና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
50 : 11

وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمۡ هُودٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۖ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا مُفۡتَرُونَ

ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን (ላክን)፡፡ አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
51 : 11

يَٰقَوۡمِ لَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ أَجۡرًاۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱلَّذِي فَطَرَنِيٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

«ሕዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይ ምንዳን አልጠይቃችሁም፡፡ ምንዳዬ በዚህ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ አታውቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
52 : 11

وَيَٰقَوۡمِ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِ يُرۡسِلِ ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡكُم مِّدۡرَارٗا وَيَزِدۡكُمۡ قُوَّةً إِلَىٰ قُوَّتِكُمۡ وَلَا تَتَوَلَّوۡاْ مُجۡرِمِينَ

«ሕዝቦቼም ሆይ! ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተጸጸቱ፡፡ ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና፡፡ ወደ ኃይላችሁም ኃይልን ይጨምርላችኋል፡፡ አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
53 : 11

قَالُواْ يَٰهُودُ مَا جِئۡتَنَا بِبَيِّنَةٖ وَمَا نَحۡنُ بِتَارِكِيٓ ءَالِهَتِنَا عَن قَوۡلِكَ وَمَا نَحۡنُ لَكَ بِمُؤۡمِنِينَ

አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም፡፡ እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም፡፡ እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም፡፡ info
التفاسير: