ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
72 : 11

قَالَتۡ يَٰوَيۡلَتَىٰٓ ءَأَلِدُ وَأَنَا۠ عَجُوزٞ وَهَٰذَا بَعۡلِي شَيۡخًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عَجِيبٞ

(እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት ይህም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
73 : 11

قَالُوٓاْ أَتَعۡجَبِينَ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِۖ رَحۡمَتُ ٱللَّهِ وَبَرَكَٰتُهُۥ عَلَيۡكُمۡ أَهۡلَ ٱلۡبَيۡتِۚ إِنَّهُۥ حَمِيدٞ مَّجِيدٞ

«ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ (በኢብራሂም) ቤተሰቦች ላይ ይሁን እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
74 : 11

فَلَمَّا ذَهَبَ عَنۡ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلرَّوۡعُ وَجَآءَتۡهُ ٱلۡبُشۡرَىٰ يُجَٰدِلُنَا فِي قَوۡمِ لُوطٍ

ከኢብራሂም ፍራቻው በሌደለትና ብስራት በመጣችለትም ጊዜ በሉጥ ሕዝቦች (ነገር) ይከራከረን ጀመር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
75 : 11

إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ لَحَلِيمٌ أَوَّٰهٞ مُّنِيبٞ

ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ አልቃሻ መላሳ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
76 : 11

يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ أَعۡرِضۡ عَنۡ هَٰذَآۖ إِنَّهُۥ قَدۡ جَآءَ أَمۡرُ رَبِّكَۖ وَإِنَّهُمۡ ءَاتِيهِمۡ عَذَابٌ غَيۡرُ مَرۡدُودٖ

«ኢብራሂም ሆይ! ከዚህ (ክርክር) ተው፡፡ እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል፡፡ እነሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው» (አሉት)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
77 : 11

وَلَمَّا جَآءَتۡ رُسُلُنَا لُوطٗا سِيٓءَ بِهِمۡ وَضَاقَ بِهِمۡ ذَرۡعٗا وَقَالَ هَٰذَا يَوۡمٌ عَصِيبٞ

መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
78 : 11

وَجَآءَهُۥ قَوۡمُهُۥ يُهۡرَعُونَ إِلَيۡهِ وَمِن قَبۡلُ كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ هَٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِي هُنَّ أَطۡهَرُ لَكُمۡۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُخۡزُونِ فِي ضَيۡفِيٓۖ أَلَيۡسَ مِنكُمۡ رَجُلٞ رَّشِيدٞ

ሕዝቦቹም ወደርሱ እየተጣደፉ መጡት፡፡ ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው፤ (አግቧቸው)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ፡፡ ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው የለምን?» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
79 : 11

قَالُواْ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا لَنَا فِي بَنَاتِكَ مِنۡ حَقّٖ وَإِنَّكَ لَتَعۡلَمُ مَا نُرِيدُ

«ከሴቶች ልጆችህ ለእኛ ምንም ጉዳይ የለንም፡፡ አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ» አሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
80 : 11

قَالَ لَوۡ أَنَّ لِي بِكُمۡ قُوَّةً أَوۡ ءَاوِيٓ إِلَىٰ رُكۡنٖ شَدِيدٖ

«በእናንተ ላይ ለኔ ኀይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
81 : 11

قَالُواْ يَٰلُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوٓاْ إِلَيۡكَۖ فَأَسۡرِ بِأَهۡلِكَ بِقِطۡعٖ مِّنَ ٱلَّيۡلِ وَلَا يَلۡتَفِتۡ مِنكُمۡ أَحَدٌ إِلَّا ٱمۡرَأَتَكَۖ إِنَّهُۥ مُصِيبُهَا مَآ أَصَابَهُمۡۚ إِنَّ مَوۡعِدَهُمُ ٱلصُّبۡحُۚ أَلَيۡسَ ٱلصُّبۡحُ بِقَرِيبٖ

«ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን፡፡ (ሕዝቦችህ) ወደ አንተ (በክፉ) አይደርሱብህም፡፡ ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሊድ፡፡ ከእናንተም አንድም (ወደኋላው) አይገላመጥ፡፡ ሚስትህ ብቻ ስትቀር፡፡ እነሆ እርሷን (እነሱን) የሚያገኛቸው ስቃይ ያገኛታልና፡፡ ቀጠሯቸው እንጋቱ ላይ ነው፡፡ ንጋቱ ቅርብ አይደለምን» አሉት፡፡ info
التفاسير: