Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
34 : 4

ٱلرِّجَالُ قَوَّٰمُونَ عَلَى ٱلنِّسَآءِ بِمَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بَعۡضَهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ وَبِمَآ أَنفَقُواْ مِنۡ أَمۡوَٰلِهِمۡۚ فَٱلصَّٰلِحَٰتُ قَٰنِتَٰتٌ حَٰفِظَٰتٞ لِّلۡغَيۡبِ بِمَا حَفِظَ ٱللَّهُۚ وَٱلَّٰتِي تَخَافُونَ نُشُوزَهُنَّ فَعِظُوهُنَّ وَٱهۡجُرُوهُنَّ فِي ٱلۡمَضَاجِعِ وَٱضۡرِبُوهُنَّۖ فَإِنۡ أَطَعۡنَكُمۡ فَلَا تَبۡغُواْ عَلَيۡهِنَّ سَبِيلًاۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيّٗا كَبِيرٗا

34. ወንዶች ለሴቶች ቋሚና የበላይ አስተዳዳሪዎች ናቸው:: አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና ወንዶች ከገንዘቦቻቸው ለሴቶች በመስጠታቸው ምክኒያት ነው:: መልካሞቹ ሴቶች ማለት ለባሎቻቸው ታዛዦች፤ አላህ ባስጠበቀው ነገር ከባሎቻቸው ሩቅ የሆነውን ጠባቂዎች ናቸው:: እነዚያን ማመፃቸውን የምትፈሩትን ሴቶች መጀመሪያ ገስጿቸው:: ከዚያም በመኝታቸው ተለዩዋቸው:: ከዚያም (በአካሎቻቸው ላይ ሳካ ሳታደርሱ) ምቷቸው:: ከታዘዟችሁ ለመጨቆን ስትሉ በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ:: አላህ የሁሉም በላይና ታላቅ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 4

وَإِنۡ خِفۡتُمۡ شِقَاقَ بَيۡنِهِمَا فَٱبۡعَثُواْ حَكَمٗا مِّنۡ أَهۡلِهِۦ وَحَكَمٗا مِّنۡ أَهۡلِهَآ إِن يُرِيدَآ إِصۡلَٰحٗا يُوَفِّقِ ٱللَّهُ بَيۡنَهُمَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا خَبِيرٗا

35. በመካከላቸውም ጭቅጭቅ መኖሩን ብትፈሩ (ብታውቁ) ከቤተሰቡና ከቤተሰቦቿ የተውጣጡ የቤተ ዘመድ ጉባኤ አዋቅሩ:: ሁለቱም እርቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማቸዋል:: አላህ ግልጽንም ሆነ ውስጥንም አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 4

۞ وَٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُشۡرِكُواْ بِهِۦ شَيۡـٔٗاۖ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنٗا وَبِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱلۡجَارِ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡجَارِ ٱلۡجُنُبِ وَٱلصَّاحِبِ بِٱلۡجَنۢبِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخۡتَالٗا فَخُورًا

36. አላህን ተገዙ:: በእርሱ ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች፣ ለቅርብ ዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለቅርብ ጎረቤት፣ ለሩቅ ጎረቤት፣ ለጎን ባልደረባ፣ ለመንገደኛ፣ እጆቻችሁ ንብረት ላደረጓቸው ባሮች መልካምን ስሩ። አላህ ኩራተኞችንና ጉረኞችን አይወድምና:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 4

ٱلَّذِينَ يَبۡخَلُونَ وَيَأۡمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلۡبُخۡلِ وَيَكۡتُمُونَ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦۗ وَأَعۡتَدۡنَا لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٗا مُّهِينٗا

37. እነዚያ የሚሰስቱ ንፉጎችና ሰዎችንም በመሰሰት (በንፍግና) የሚያዝዙ አላህ ከችሮታው የሰጣቸውን ጸጋ የሚደብቁ ብርቱን ቅጣት ይቀጣቸዋል። ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል። info
التفاسير: