Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
163 : 4

۞ إِنَّآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ كَمَآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ نُوحٖ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ مِنۢ بَعۡدِهِۦۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ وَٱلۡأَسۡبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَٰرُونَ وَسُلَيۡمَٰنَۚ وَءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ زَبُورٗا

163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ ኑህና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነብያት መልዕክታችንን እንዳወረድን ሁሉ ወደ አንተም ቁርኣንን አወረድን:: ወደ ነብዩ ኢብራሂም፤ ወደ ነብዩ ኢስማኢልም፤ ወደ ነብዩ ኢስሃቅም፤ ወደ ነብዩ የዕቆብም፤ ወደ ነገዶችም፤ ወደ ነብዩ ዒሳም፤ ወደ ነብዩ አዩብም፤ ወደ ነብዩ ዩኑስም፤ ወደ ነብዩ ሃሩንና ወደ ነብዩ ሱለይማን አወረድን:: ለነብዩ ዳውድም ዘቡርን ሰጠነው:: info
التفاسير:

external-link copy
164 : 4

وَرُسُلٗا قَدۡ قَصَصۡنَٰهُمۡ عَلَيۡكَ مِن قَبۡلُ وَرُسُلٗا لَّمۡ نَقۡصُصۡهُمۡ عَلَيۡكَۚ وَكَلَّمَ ٱللَّهُ مُوسَىٰ تَكۡلِيمٗا

164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚህም በፊት በአንተ ላይ በእርግጥ የተረክናቸውን መልዕክተኞች ባንተ ላይም ያልተረክናቸውንም መልዕክተኞች እንደላክን ሁሉ አንተን ላክንህ:: አላህ ነብዩ ሙሳንም ማነጋገርን አነጋገረው:: info
التفاسير:

external-link copy
165 : 4

رُّسُلٗا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةُۢ بَعۡدَ ٱلرُّسُلِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمٗا

165. ከመልዕክተኞች በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ ምንም አስረጂ እንዳይኖራቸው አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርገን መልዕክተኞችን ላክን:: አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
166 : 4

لَّٰكِنِ ٱللَّهُ يَشۡهَدُ بِمَآ أَنزَلَ إِلَيۡكَۖ أَنزَلَهُۥ بِعِلۡمِهِۦۖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَشۡهَدُونَۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًا

166. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ግን ባንተ ላይ ባወረደው ቁርኣን ይመሰክራል:: በእውቀቱ አወረደው:: መላዕክቱም ይመሰክራሉ:: መስካሪነትም በአላህ ብቻ በቃ:: info
التفاسير:

external-link copy
167 : 4

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ قَدۡ ضَلُّواْ ضَلَٰلَۢا بَعِيدًا

167. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድም ሰዎችን ያገዱ ሰዎች ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳቱ:: info
التفاسير:

external-link copy
168 : 4

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَظَلَمُواْ لَمۡ يَكُنِ ٱللَّهُ لِيَغۡفِرَ لَهُمۡ وَلَا لِيَهۡدِيَهُمۡ طَرِيقًا

168. እነዚያ የካዱና የበደሉ አላህ የሚምራቸውና ቅን መንገድን የሚመራቸው አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
169 : 4

إِلَّا طَرِيقَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٗا

169. ግን በውስጧ ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ የገሀነምን መንገድ ይመራቸዋል:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
170 : 4

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدۡ جَآءَكُمُ ٱلرَّسُولُ بِٱلۡحَقِّ مِن رَّبِّكُمۡ فَـَٔامِنُواْ خَيۡرٗا لَّكُمۡۚ وَإِن تَكۡفُرُواْ فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا

170. እናንተ ሰዎች ሆይ! መልዕክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ:: እናም ባመጣው እመኑ ለእናንተ የተሻለ ይሆናል:: በአላህ ብትክዱም እሱን (ቅንጣት) አትጎዱትም:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير: