Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
92 : 4

وَمَا كَانَ لِمُؤۡمِنٍ أَن يَقۡتُلَ مُؤۡمِنًا إِلَّا خَطَـٔٗاۚ وَمَن قَتَلَ مُؤۡمِنًا خَطَـٔٗا فَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مُّؤۡمِنَةٖ وَدِيَةٞ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦٓ إِلَّآ أَن يَصَّدَّقُواْۚ فَإِن كَانَ مِن قَوۡمٍ عَدُوّٖ لَّكُمۡ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مُّؤۡمِنَةٖۖ وَإِن كَانَ مِن قَوۡمِۭ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُم مِّيثَٰقٞ فَدِيَةٞ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ وَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مُّؤۡمِنَةٖۖ فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ شَهۡرَيۡنِ مُتَتَابِعَيۡنِ تَوۡبَةٗ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا

92. አማኝ በስህተት ካልሆነ በስተቀር አማኝን መግደል አይገባዉም:: አማኝን በስህተት የገደለም አማኝ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ምህረት ካላደረጉለት በስተቀር ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማ መክፈል አለበት:: ተገዳዩ ምዕመን ሆኖ ለእናንተ ጠላት ከሆኑ ህዝቦች ዘንድ ቢሆንም አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ተገዳዩ በእናንተ እና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ካላቸዉም ህዝቦች ጋር ቢሆን ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማና አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ይህንን ያላገኘም በተከታታይ ሁለት ወሮችን መፆም አለበት:: ከአላህ የሆነ ጸጸት (ለመቀበል ደነገገላችሁ::) አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
93 : 4

وَمَن يَقۡتُلۡ مُؤۡمِنٗا مُّتَعَمِّدٗا فَجَزَآؤُهُۥ جَهَنَّمُ خَٰلِدٗا فِيهَا وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِ وَلَعَنَهُۥ وَأَعَدَّ لَهُۥ عَذَابًا عَظِيمٗا

93. አማኝን አስቦ የሚገድል ቅጣቱ በውስጧ ዘወታሪ ሲሆን ገሀነም ናት:: አላህ በእርሱ ላይ ተቆጣ:: ረገመዉም:: ለእርሱ ከባድ ቅጣትን አዘጋጀቶለታል:: info
التفاسير:

external-link copy
94 : 4

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا ضَرَبۡتُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَتَبَيَّنُواْ وَلَا تَقُولُواْ لِمَنۡ أَلۡقَىٰٓ إِلَيۡكُمُ ٱلسَّلَٰمَ لَسۡتَ مُؤۡمِنٗا تَبۡتَغُونَ عَرَضَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا فَعِندَ ٱللَّهِ مَغَانِمُ كَثِيرَةٞۚ كَذَٰلِكَ كُنتُم مِّن قَبۡلُ فَمَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمۡ فَتَبَيَّنُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٗا

94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ ለመዋጋት በተጓዛችሁ ጊዜ አረጋግጡ:: ሰላምታን ወደ እናንተ ላቀረበ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም የምትፈልጉ ሆናችሁ «ትክክለኛ አማኝ አይደለህም።» አትበሉት:: አላህ ዘንድ ብዙ ምርኮዎች አሉና:: እናንተም ከዚህ በፊት ልክ እንደዚሁ ነበራችሁ:: አላህ በእናንተ ላይ ለገሰ:: ስለዚህም አረጋግጡ:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير: