Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası.

Səhifənin rəqəmi: 21:2 close

external-link copy
142 : 2

۞ سَيَقُولُ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَ ٱلنَّاسِ مَا وَلَّىٰهُمۡ عَن قِبۡلَتِهِمُ ٱلَّتِي كَانُواْ عَلَيۡهَاۚ قُل لِّلَّهِ ٱلۡمَشۡرِقُ وَٱلۡمَغۡرِبُۚ يَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

142. ቂል የህብረተሰብ ክፍሎች «ከዚያች ከነበሩባት ቂብላቸው (አቅጣጫቻቸው) ምን አዞራቸው?» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው:: የሻውንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
143 : 2

وَكَذَٰلِكَ جَعَلۡنَٰكُمۡ أُمَّةٗ وَسَطٗا لِّتَكُونُواْ شُهَدَآءَ عَلَى ٱلنَّاسِ وَيَكُونَ ٱلرَّسُولُ عَلَيۡكُمۡ شَهِيدٗاۗ وَمَا جَعَلۡنَا ٱلۡقِبۡلَةَ ٱلَّتِي كُنتَ عَلَيۡهَآ إِلَّا لِنَعۡلَمَ مَن يَتَّبِعُ ٱلرَّسُولَ مِمَّن يَنقَلِبُ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِۚ وَإِن كَانَتۡ لَكَبِيرَةً إِلَّا عَلَى ٱلَّذِينَ هَدَى ٱللَّهُۗ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَٰنَكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِٱلنَّاسِ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ

143. እንደዚሁም (እንደመራናችሁ) ሁሉ በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልዕክተኛዉም (ሙሐመድ) በእናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ መካከለኞች (ምርጥ) ማህበረሰብ (ህዝቦች) አደረግናችሁ:: ያችንም በእርሷ ላይ የነበርክባትን አቅጣጫ መልዕክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ልናውቅ (ልንለይ) (ልንገልጽ) እንጂ ቂብላን አላደረግናትም:: እርሷም በዚያ አላህ በመራቸው ሰዎች ላይ በስተቀር በእርግጥ ከባድ ናት:: አላህም እምነታችሁን (ስግደታችሁን) የሚያጠፋ አይደለም:: አላህም ለሰዎች በጣም ሩህሩህና አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
144 : 2

قَدۡ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجۡهِكَ فِي ٱلسَّمَآءِۖ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبۡلَةٗ تَرۡضَىٰهَاۚ فَوَلِّ وَجۡهَكَ شَطۡرَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۚ وَحَيۡثُ مَا كُنتُمۡ فَوَلُّواْ وُجُوهَكُمۡ شَطۡرَهُۥۗ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ لَيَعۡلَمُونَ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّهِمۡۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعۡمَلُونَ

144. የፊትህን ወደ ሰማይ ማንጋጠጥክን በእርግጥ ተመልክተናል:: እናም ወደ ምትወዳት (ከዕባ) ቂብላ እናዞርሃለን:: ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙር:: (ሙስሊሞች ሆይ!) የትም ስፍራ ብትሆኑ ስትሰግዱ ፊቶቻችሁን ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙሩ:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: አላህ ከሚሰሩት ስራ ዘንጊ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
145 : 2

وَلَئِنۡ أَتَيۡتَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ بِكُلِّ ءَايَةٖ مَّا تَبِعُواْ قِبۡلَتَكَۚ وَمَآ أَنتَ بِتَابِعٖ قِبۡلَتَهُمۡۚ وَمَا بَعۡضُهُم بِتَابِعٖ قِبۡلَةَ بَعۡضٖۚ وَلَئِنِ ٱتَّبَعۡتَ أَهۡوَآءَهُم مِّنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلۡعِلۡمِ إِنَّكَ إِذٗا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

145.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ መጽሐፍን ለተሰጡት ሕዝቦች የምትችለውን ያህል ተዓምር (መረጃ) ሁሉ ብታቀርብላቸው እንኳ ቂብላህን አይከተሉም:: አንተም ቂብላቸውን ተከታይ አይደለህም:: ከፊላቸዉም የከፊሉን ቂብላ አይከተሉም:: ከእውቀትም (ራእይ) ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ያን ጊዜ አንተ ከአጥፊዎች ትሆናለህ:: info
التفاسير: