Qurani Kərimin mənaca tərcüməsi - Amhar dilinə tərcümə - Afrika Akademiyası.

external-link copy
143 : 2

وَكَذَٰلِكَ جَعَلۡنَٰكُمۡ أُمَّةٗ وَسَطٗا لِّتَكُونُواْ شُهَدَآءَ عَلَى ٱلنَّاسِ وَيَكُونَ ٱلرَّسُولُ عَلَيۡكُمۡ شَهِيدٗاۗ وَمَا جَعَلۡنَا ٱلۡقِبۡلَةَ ٱلَّتِي كُنتَ عَلَيۡهَآ إِلَّا لِنَعۡلَمَ مَن يَتَّبِعُ ٱلرَّسُولَ مِمَّن يَنقَلِبُ عَلَىٰ عَقِبَيۡهِۚ وَإِن كَانَتۡ لَكَبِيرَةً إِلَّا عَلَى ٱلَّذِينَ هَدَى ٱللَّهُۗ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَٰنَكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِٱلنَّاسِ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ

143. እንደዚሁም (እንደመራናችሁ) ሁሉ በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልዕክተኛዉም (ሙሐመድ) በእናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ መካከለኞች (ምርጥ) ማህበረሰብ (ህዝቦች) አደረግናችሁ:: ያችንም በእርሷ ላይ የነበርክባትን አቅጣጫ መልዕክተኛውን የሚከተለውን ሰው ወደ ክህደት ከሚመለሰው ሰው ልናውቅ (ልንለይ) (ልንገልጽ) እንጂ ቂብላን አላደረግናትም:: እርሷም በዚያ አላህ በመራቸው ሰዎች ላይ በስተቀር በእርግጥ ከባድ ናት:: አላህም እምነታችሁን (ስግደታችሁን) የሚያጠፋ አይደለም:: አላህም ለሰዎች በጣም ሩህሩህና አዛኝ ነው:: info
التفاسير: