Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译 - 穆罕默德·萨迪格

አት ተጋቡን

external-link copy
1 : 64

يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ لَهُ ٱلۡمُلۡكُ وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

በሰማያት ውስጥ ያለው በምድርም ውስጥ ያለው ሁሉ ለአላህ ያሞግሳል፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ለእርሱ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 64

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ فَمِنكُمۡ كَافِرٞ وَمِنكُم مُّؤۡمِنٞۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ

እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከእናንተም ከሓዲ አልለ፡፡ ከእናንተም አማኝ አልለ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 64

خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّ وَصَوَّرَكُمۡ فَأَحۡسَنَ صُوَرَكُمۡۖ وَإِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ

ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ፡፡ ቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም አሳመረ፡፡ መመለሻችሁም ወደእርሱ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 64

يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَيَعۡلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعۡلِنُونَۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል፡፡ አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 64

أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ نَبَؤُاْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَبۡلُ فَذَاقُواْ وَبَالَ أَمۡرِهِمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

የእነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክሕደታቸውን ቅጣት የቀመሱ ሕዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለእነሱም አሳማሚ ቅጣት አልላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 64

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُۥ كَانَت تَّأۡتِيهِمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَقَالُوٓاْ أَبَشَرٞ يَهۡدُونَنَا فَكَفَرُواْ وَتَوَلَّواْۖ وَّٱسۡتَغۡنَى ٱللَّهُۚ وَٱللَّهُ غَنِيٌّ حَمِيدٞ

ይህ (ቅጣት) እርሱ መልክተኞቻቸው በአስረጂዎች ይመጡባቸው ስለ ነበሩ «ሰዎችም ይመሩናልን?» ስላሉና ስለካዱ (ከእምነት) ስለ ዞሩም ነው፡፡ አላህም (ከእነሱ እምነት) ተብቃቃ፡፡ አላህም ተብቃቂ ምስጉን ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 64

زَعَمَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَن لَّن يُبۡعَثُواْۚ قُلۡ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتُبۡعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلۡتُمۡۚ وَذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ

እነዚያ የካዱትን በፍጹም የማይቀሰሱ መኾናቸውን አሰቡ፡፡ «አይደለም በጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ ከዚያም በሠራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው፡፡» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 64

فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلنُّورِ ٱلَّذِيٓ أَنزَلۡنَاۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

በአላህና በመልክተኛውም፡፡ በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑ፡፡ «አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው» (በላቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 64

يَوۡمَ يَجۡمَعُكُمۡ لِيَوۡمِ ٱلۡجَمۡعِۖ ذَٰلِكَ يَوۡمُ ٱلتَّغَابُنِۗ وَمَن يُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ وَيَعۡمَلۡ صَٰلِحٗا يُكَفِّرۡ عَنۡهُ سَيِّـَٔاتِهِۦ وَيُدۡخِلۡهُ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

ለመሰብሰቢያ ቀን የሚሰበስብባችሁን ቀን (አስታውሱ)፤ ይህ የመጎዳዳት (መግለጫ) ቀን ነው፡፡ በአላህም የሚያምን ሰው መልካምንም የሚሠራ ከርሱ ኃጢአቶቹን ይሰርይለታል፤ (ይፍቅለታል)፤ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባዋል፤ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 64

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ

እነዚያም የካዱና በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ እነዚያ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲኾኑ የእሳት ጓዶች ናቸው፤ መመለሻቸውም ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
11 : 64

مَآ أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَمَن يُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ يَهۡدِ قَلۡبَهُۥۚ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ

ከመከራም (ማንንም) አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን (ለትዕግስት) ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 64

وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَۚ فَإِن تَوَلَّيۡتُمۡ فَإِنَّمَا عَلَىٰ رَسُولِنَا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ

አላህንም ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትዞሩም (መልክተኛውን አትጎዱም)፤ በመልክተኛውም ላይ ያለበት ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 64

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

አላህ ከርሱ በቀር አምላክ የለም፤ በአላህም ላይ አማኞቹ ይመኩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 64

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّ مِنۡ أَزۡوَٰجِكُمۡ وَأَوۡلَٰدِكُمۡ عَدُوّٗا لَّكُمۡ فَٱحۡذَرُوهُمۡۚ وَإِن تَعۡفُواْ وَتَصۡفَحُواْ وَتَغۡفِرُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ

እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው፤ ይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብተምሩዋቸውም አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 64

إِنَّمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَأَوۡلَٰدُكُمۡ فِتۡنَةٞۚ وَٱللَّهُ عِندَهُۥٓ أَجۡرٌ عَظِيمٞ

ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው፤ አላህም እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አልለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 64

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُمۡ وَٱسۡمَعُواْ وَأَطِيعُواْ وَأَنفِقُواْ خَيۡرٗا لِّأَنفُسِكُمۡۗ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفۡسِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

አላህንም የቻላችሁትን የክል ፍሩት፤ ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን (ይሰጣችኋልና)፤ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 64

إِن تُقۡرِضُواْ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا يُضَٰعِفۡهُ لَكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ شَكُورٌ حَلِيمٌ

ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ (ምንዳውን) ለናንተ ይደራርበዋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህም አመስጋኝ ታጋሽ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 64

عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

ሩቁን ምስጢር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ info
التفاسير: