Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译 - 穆罕默德·萨迪格

አን ነጅም

external-link copy
1 : 53

وَٱلنَّجۡمِ إِذَا هَوَىٰ

በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 53

مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمۡ وَمَا غَوَىٰ

ባልደረባችሁ (ነቢያችን ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 53

وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلۡهَوَىٰٓ

ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 53

إِنۡ هُوَ إِلَّا وَحۡيٞ يُوحَىٰ

እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 53

عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلۡقُوَىٰ

ኀይሎቹ ብርቱው አስተማረው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 53

ذُو مِرَّةٖ فَٱسۡتَوَىٰ

የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 53

وَهُوَ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡأَعۡلَىٰ

እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 53

ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ

ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 53

فَكَانَ قَابَ قَوۡسَيۡنِ أَوۡ أَدۡنَىٰ

(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 53

فَأَوۡحَىٰٓ إِلَىٰ عَبۡدِهِۦ مَآ أَوۡحَىٰ

ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 53

مَا كَذَبَ ٱلۡفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ

(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 53

أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ

ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
13 : 53

وَلَقَدۡ رَءَاهُ نَزۡلَةً أُخۡرَىٰ

በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 53

عِندَ سِدۡرَةِ ٱلۡمُنتَهَىٰ

በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 53

عِندَهَا جَنَّةُ ٱلۡمَأۡوَىٰٓ

እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 53

إِذۡ يَغۡشَى ٱلسِّدۡرَةَ مَا يَغۡشَىٰ

ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 53

مَا زَاغَ ٱلۡبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ

ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 53

لَقَدۡ رَأَىٰ مِنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ

ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 53

أَفَرَءَيۡتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلۡعُزَّىٰ

አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
20 : 53

وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ

ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?) (የላቸውም)። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 53

أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلۡأُنثَىٰ

ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 53

تِلۡكَ إِذٗا قِسۡمَةٞ ضِيزَىٰٓ

ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍፍል ናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 53

إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٞ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهۡوَى ٱلۡأَنفُسُۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلۡهُدَىٰٓ

እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 53

أَمۡ لِلۡإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ

ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን? info
التفاسير:

external-link copy
25 : 53

فَلِلَّهِ ٱلۡأٓخِرَةُ وَٱلۡأُولَىٰ

መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 53

۞ وَكَم مِّن مَّلَكٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ

በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 53

إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ لَيُسَمُّونَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ تَسۡمِيَةَ ٱلۡأُنثَىٰ

እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 53

وَمَا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّۖ وَإِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغۡنِي مِنَ ٱلۡحَقِّ شَيۡـٔٗا

ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 53

فَأَعۡرِضۡ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكۡرِنَا وَلَمۡ يُرِدۡ إِلَّا ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا

ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 53

ذَٰلِكَ مَبۡلَغُهُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱهۡتَدَىٰ

ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 53

وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ بِمَا عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ بِٱلۡحُسۡنَى

በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊመነዳ (ሊቀጣ) እነዚያን ያሳመሩትንም በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ (ነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 53

ٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلۡمَغۡفِرَةِۚ هُوَ أَعۡلَمُ بِكُمۡ إِذۡ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَإِذۡ أَنتُمۡ أَجِنَّةٞ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡۖ فَلَا تُزَكُّوٓاْ أَنفُسَكُمۡۖ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ

(እነርሱ) እነዚያ የኃጢኣትን ታላለቆችና አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን ትናንሾቹ (የሚማሩ) ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ ሽሎች በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በናንተ (ኹነታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ነፍሶቻችሁንም አታወድሱ እርሱ የሚፈራውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 53

أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي تَوَلَّىٰ

ያንን (ከእምነት) የዞረውን አየህን? info
التفاسير:

external-link copy
34 : 53

وَأَعۡطَىٰ قَلِيلٗا وَأَكۡدَىٰٓ

ጥቂትን የሰጠውንና ያቋረጠውንም (አየህን?) info
التفاسير:

external-link copy
35 : 53

أَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلۡغَيۡبِ فَهُوَ يَرَىٰٓ

የሩቁ ምስጢር ዕውቀት እርሱ ዘንድ አልለን? ስለዚህ እርሱ ያያልን? info
التفاسير:

external-link copy
36 : 53

أَمۡ لَمۡ يُنَبَّأۡ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ

ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? info
التفاسير:

external-link copy
37 : 53

وَإِبۡرَٰهِيمَ ٱلَّذِي وَفَّىٰٓ

በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) info
التفاسير:

external-link copy
38 : 53

أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰ

(እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 53

وَأَن لَّيۡسَ لِلۡإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ

ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 53

وَأَنَّ سَعۡيَهُۥ سَوۡفَ يُرَىٰ

ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 53

ثُمَّ يُجۡزَىٰهُ ٱلۡجَزَآءَ ٱلۡأَوۡفَىٰ

ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 53

وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلۡمُنتَهَىٰ

መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 53

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَضۡحَكَ وَأَبۡكَىٰ

እነሆ እርሱም አስሳቀ፣ አስለቀሰም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 53

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَمَاتَ وَأَحۡيَا

እነሆ እርሱም ገደለ፣ አስነሳም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
45 : 53

وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰ

እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
46 : 53

مِن نُّطۡفَةٍ إِذَا تُمۡنَىٰ

ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 53

وَأَنَّ عَلَيۡهِ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰ

የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
48 : 53

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَغۡنَىٰ وَأَقۡنَىٰ

እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
49 : 53

وَأَنَّهُۥ هُوَ رَبُّ ٱلشِّعۡرَىٰ

እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
50 : 53

وَأَنَّهُۥٓ أَهۡلَكَ عَادًا ٱلۡأُولَىٰ

እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
51 : 53

وَثَمُودَاْ فَمَآ أَبۡقَىٰ

ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
52 : 53

وَقَوۡمَ نُوحٖ مِّن قَبۡلُۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ هُمۡ أَظۡلَمَ وَأَطۡغَىٰ

በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
53 : 53

وَٱلۡمُؤۡتَفِكَةَ أَهۡوَىٰ

የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
54 : 53

فَغَشَّىٰهَا مَا غَشَّىٰ

ያለበሳትንም አለበሳት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 53

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ

ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ? info
التفاسير:

external-link copy
56 : 53

هَٰذَا نَذِيرٞ مِّنَ ٱلنُّذُرِ ٱلۡأُولَىٰٓ

ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 53

أَزِفَتِ ٱلۡأٓزِفَةُ

ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 53

لَيۡسَ لَهَا مِن دُونِ ٱللَّهِ كَاشِفَةٌ

ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 53

أَفَمِنۡ هَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ تَعۡجَبُونَ

ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
60 : 53

وَتَضۡحَكُونَ وَلَا تَبۡكُونَ

ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን? info
التفاسير:

external-link copy
61 : 53

وَأَنتُمۡ سَٰمِدُونَ

እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
62 : 53

فَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ وَٱعۡبُدُواْ۩

ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡ {1} info

{1} ኢዝህ አንድ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱትላዋ) ይደረጋል።

التفاسير: