Bản dịch ý nghĩa nội dung Qur'an - 阿姆哈拉语翻译 - 穆罕默德·萨迪格

ሁድ

external-link copy
1 : 11

الٓرۚ كِتَٰبٌ أُحۡكِمَتۡ ءَايَٰتُهُۥ ثُمَّ فُصِّلَتۡ مِن لَّدُنۡ حَكِيمٍ خَبِيرٍ

አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 11

أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنۡهُ نَذِيرٞ وَبَشِيرٞ

(እንዲህ በላቸው)፡- «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ እኔ ለእናንተ ከርሱ (የተላክሁ) አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
3 : 11

وَأَنِ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِ يُمَتِّعۡكُم مَّتَٰعًا حَسَنًا إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى وَيُؤۡتِ كُلَّ ذِي فَضۡلٖ فَضۡلَهُۥۖ وَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٖ كَبِيرٍ

ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋልና፡፡ የትሩፋትንም ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳውን) ይሰጠዋል፡፡ ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 11

إِلَى ٱللَّهِ مَرۡجِعُكُمۡۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 11

أَلَآ إِنَّهُمۡ يَثۡنُونَ صُدُورَهُمۡ لِيَسۡتَخۡفُواْ مِنۡهُۚ أَلَا حِينَ يَسۡتَغۡشُونَ ثِيَابَهُمۡ يَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

ንቁ! እነሱ ከእርሱ (ከአላህ) ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ፡፡ ንቁ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትን የሚገልጹትንም ሁሉ ያውቃል፡፡ እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡ info
التفاسير: