Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси

Бет рақами:close

external-link copy
43 : 16

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ إِلَّا رِجَالٗا نُّوحِيٓ إِلَيۡهِمۡۖ فَسۡـَٔلُوٓاْ أَهۡلَ ٱلذِّكۡرِ إِن كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም:: (ሰዎች ሆይ! ) የማታውቁም ከሆናችሁ የዕውቀትን ባለቤቶችን ጠይቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 16

بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِۗ وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلذِّكۡرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ

44. በግልጽ ማስረጃዎችና በመጽሐፍ ላክናቸው። ለሰዎችም ወደ እነርሱ የተወረደላቸውን ፍች ትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ወደ አንተ ቁርኣንን አወረድን:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 16

أَفَأَمِنَ ٱلَّذِينَ مَكَرُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن يَخۡسِفَ ٱللَّهُ بِهِمُ ٱلۡأَرۡضَ أَوۡ يَأۡتِيَهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ

45. እነዚያን መጥፎዎችን የዶለቱ ሰዎች አላህ በእነርሱ ምድርን የሚያስዉጣቸው ወይም ከማያውቁት ሥፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን? info
التفاسير:

external-link copy
46 : 16

أَوۡ يَأۡخُذَهُمۡ فِي تَقَلُّبِهِمۡ فَمَا هُم بِمُعۡجِزِينَ

46. ወይም ከአገር ወደ አገር በሚዛወሩበት ጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ የሚይዛቸው መሆኑን አይፈሩምን? እነርሱም አሸናፊዎች አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 16

أَوۡ يَأۡخُذَهُمۡ عَلَىٰ تَخَوُّفٖ فَإِنَّ رَبَّكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٌ

47. ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን? ጌታችሁም ሩሕሩህና አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 16

أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَىٰ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ مِن شَيۡءٖ يَتَفَيَّؤُاْ ظِلَٰلُهُۥ عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَٱلشَّمَآئِلِ سُجَّدٗا لِّلَّهِ وَهُمۡ دَٰخِرُونَ

48. ወደዚያ ከማንኛዉም ነገር አላህ ወደ ፈጠረው ጥላዎቹ እነርሱም የተዋረዱ ሲሆኑ ለአላህ ሰጋጆች ሆነው ከቀኝ እና ከግራዎች ወደ ሚዛወሩት አላዩምን? info
التفاسير:

external-link copy
49 : 16

وَلِلَّهِۤ يَسۡجُدُۤ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ مِن دَآبَّةٖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَهُمۡ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ

49. በሰማያትና በምድር ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መላዕክትም ለአላህ ብቻ ይሰግዳሉ:: እነርሱም አይኮሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 16

يَخَافُونَ رَبَّهُم مِّن فَوۡقِهِمۡ وَيَفۡعَلُونَ مَا يُؤۡمَرُونَ۩

50. ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል:: የታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ (ይፈጽማሉ):: {1} info

{1} አዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁድ አትላዋ) ይደረጋል።

التفاسير:

external-link copy
51 : 16

۞ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓاْ إِلَٰهَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ فَإِيَّٰيَ فَٱرۡهَبُونِ

51. አላህም አለ: «ሁለት አማልክት አትያዙ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔን ብቻ ፍሩኝ።» info
التفاسير:

external-link copy
52 : 16

وَلَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَهُ ٱلدِّينُ وَاصِبًاۚ أَفَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَتَّقُونَ

52. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: አምልኮም ዘወትር ለርሱ ብቻ ነው:: ከአላህ ሌላ ያለን ትፈራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
53 : 16

وَمَا بِكُم مِّن نِّعۡمَةٖ فَمِنَ ٱللَّهِۖ ثُمَّ إِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فَإِلَيۡهِ تَجۡـَٔرُونَ

53. ማንኛዉም በናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ብቻ ነው። ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደ እርሱ ብቻ ትጮሀላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
54 : 16

ثُمَّ إِذَا كَشَفَ ٱلضُّرَّ عَنكُمۡ إِذَا فَرِيقٞ مِّنكُم بِرَبِّهِمۡ يُشۡرِكُونَ

54. ከዚያም ከናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከናንተ የሆኑ ቡድኖች ወዲያውኑ በጌታችሁ ጣዖትን ያጋራሉ:: info
التفاسير: