Қуръони Карим маъноларининг таржимаси - Амҳарийча таржима - Африка академияси

አን-ነሕል

external-link copy
1 : 16

أَتَىٰٓ أَمۡرُ ٱللَّهِ فَلَا تَسۡتَعۡجِلُوهُۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

1. (ከሓዲያን ሆይ!)፤ የአላህ ትዕዛዝ መጣ ስለዚህ አታጣድፉት:: አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ:: ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 16

يُنَزِّلُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنۡ أَمۡرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦٓ أَنۡ أَنذِرُوٓاْ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ

2. ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ መላዕክትን ከራዕይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል:: «ከሓዲያንን በቅጣት አስጠንቅቁ:: እነሆ ከእኔ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ፍሩኝም።» ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 16

خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۚ تَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

3. ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ :: ከፍም አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 16

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِن نُّطۡفَةٖ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٞ مُّبِينٞ

4.ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው:: ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ ትንሣኤን በመካድ ግልጽ ተከራካሪ ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 16

وَٱلۡأَنۡعَٰمَ خَلَقَهَاۖ لَكُمۡ فِيهَا دِفۡءٞ وَمَنَٰفِعُ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ

5. (ሰዎች ሆይ!) ግመልን፤ ከብትን፤ ፍየልንም፤ በእርሷ ብርድ መከላከያ ሙቀትና ሌሎች ጥቅሞችም ያሉባት ስትሆን ለእናንተ ፈጠረላችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ (ትመገባላችሁ):: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 16

وَلَكُمۡ فِيهَا جَمَالٌ حِينَ تُرِيحُونَ وَحِينَ تَسۡرَحُونَ

6. በእርሷም ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜና ጧት ወደ ግጦሽ ቦታዋ በምታሰማሯት ወቅት ለእናንተ ውበት አለላችሁ። info
التفاسير: