قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

صفحہ نمبر:close

external-link copy
77 : 27

وَإِنَّهُۥ لَهُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ

77. እርሱም ለአማኞች ብቸኛ መምሪያና እዝነት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
78 : 27

إِنَّ رَبَّكَ يَقۡضِي بَيۡنَهُم بِحُكۡمِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡعَلِيمُ

78. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፤ እርሱም ሁሉን አሸናፊዉና አዋቂው ነው። info
التفاسير:

external-link copy
79 : 27

فَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۖ إِنَّكَ عَلَى ٱلۡحَقِّ ٱلۡمُبِينِ

79. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህም ላይ ተጠጋ:: አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና። info
التفاسير:

external-link copy
80 : 27

إِنَّكَ لَا تُسۡمِعُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَلَا تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوۡاْ مُدۡبِرِينَ

80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ሙታንን አታሰማም። ደንቆሮዎችንም የሚተው ሆነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም። info
التفاسير:

external-link copy
81 : 27

وَمَآ أَنتَ بِهَٰدِي ٱلۡعُمۡيِ عَن ضَلَٰلَتِهِمۡۖ إِن تُسۡمِعُ إِلَّا مَن يُؤۡمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُم مُّسۡلِمُونَ

81.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ልበ ዕውሮችን ከጥመታቸው አቅኚ አይደለህም:: እነዚያን በአናቅጻችን በትክክል የሚያምኑትን እንጂ አታሰማም:: እነርሱ ፍጹም ታዛዦች (ሙስሊሞች) ናቸውና። info
التفاسير:

external-link copy
82 : 27

۞ وَإِذَا وَقَعَ ٱلۡقَوۡلُ عَلَيۡهِمۡ أَخۡرَجۡنَا لَهُمۡ دَآبَّةٗ مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ تُكَلِّمُهُمۡ أَنَّ ٱلنَّاسَ كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا لَا يُوقِنُونَ

82. በእነርሱም ላይ የቅጣት ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአናቅጻችን የማያረጋግጡ እንደነበሩ የምትነግራቸውን እንስሳ ለእነርሱ ከምድር እናወጣላቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 27

وَيَوۡمَ نَحۡشُرُ مِن كُلِّ أُمَّةٖ فَوۡجٗا مِّمَّن يُكَذِّبُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُمۡ يُوزَعُونَ

83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦቹም ሁሉ በአናቅጽ የሚያስተባብሉትን ቡድኖች የምንሰበስብበትን ቀን አስታውስ:: እነርሱም ይከመከማሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 27

حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُو قَالَ أَكَذَّبۡتُم بِـَٔايَٰتِي وَلَمۡ تُحِيطُواْ بِهَا عِلۡمًا أَمَّاذَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

84. በመጡም ጊዜ (አላህ) ይላቸዋል፡ «በአንቀጾቼ እርሷን በማወቅ ያላዳረሳችሁ ስትሆኑ አስተባበላችሁን? ወይስ ምንን ትሰሩ ነበራችሁ?» info
التفاسير:

external-link copy
85 : 27

وَوَقَعَ ٱلۡقَوۡلُ عَلَيۡهِم بِمَا ظَلَمُواْ فَهُمۡ لَا يَنطِقُونَ

85. በመበደላቸዉም ምክኒያት በእነርሱ ላይ ቃሉ ይፈጸምባቸዋል:: እነርሱም አይናገሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 27

أَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا جَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِيَسۡكُنُواْ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبۡصِرًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ

86. እኛ ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንደሚያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን? ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ አያሌ ተዓምራት አሉበት:: info
التفاسير:

external-link copy
87 : 27

وَيَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَفَزِعَ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا مَن شَآءَ ٱللَّهُۚ وَكُلٌّ أَتَوۡهُ دَٰخِرِينَ

87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉትና በምድርም ውስጥ ያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ። ሁሉም የተናነሱ ሆነዉም ወደ እርሱ ይመጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
88 : 27

وَتَرَى ٱلۡجِبَالَ تَحۡسَبُهَا جَامِدَةٗ وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ ٱلسَّحَابِۚ صُنۡعَ ٱللَّهِ ٱلَّذِيٓ أَتۡقَنَ كُلَّ شَيۡءٍۚ إِنَّهُۥ خَبِيرُۢ بِمَا تَفۡعَلُونَ

88. ጋራዎችንም እርሷ እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትሆን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያለህ፤ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት:: እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው:: info
التفاسير: