قرآن کریم کے معانی کا ترجمہ - امہاری ترجمہ - افریقہ اکیڈمی

صفحہ نمبر:close

external-link copy
56 : 27

۞ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَخۡرِجُوٓاْ ءَالَ لُوطٖ مِّن قَرۡيَتِكُمۡۖ إِنَّهُمۡ أُنَاسٞ يَتَطَهَّرُونَ

56. የህዝቦቹም መልስ «የሉጥን ቤተሰቦች ከከተማችሁ አውጡ:: እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና።» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም። info
التفاسير:

external-link copy
57 : 27

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ قَدَّرۡنَٰهَا مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ

57. እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንን:: ሚስቱ ብቻ ስትቀር:: እርሷማ በጥፋቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ አደረግናት:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 27

وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَسَآءَ مَطَرُ ٱلۡمُنذَرِينَ

58. በእነርሱም ላይ የድንጋይ ዝናብን አዘነብንባቸው:: የተስፈራሪዎቹም የቅጣት ዝናብ ከፋ። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 27

قُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ وَسَلَٰمٌ عَلَىٰ عِبَادِهِ ٱلَّذِينَ ٱصۡطَفَىٰٓۗ ءَآللَّهُ خَيۡرٌ أَمَّا يُشۡرِكُونَ

59. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሁልጊዜም ሰላም ይውረድ:: አላህ በላጭ ነውን? ወይስ ያ በእርሱ የሚያጋሩት ጣዖት?» በል። info
التفاسير:

external-link copy
60 : 27

أَمَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَنۢبَتۡنَا بِهِۦ حَدَآئِقَ ذَاتَ بَهۡجَةٖ مَّا كَانَ لَكُمۡ أَن تُنۢبِتُواْ شَجَرَهَآۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ بَلۡ هُمۡ قَوۡمٞ يَعۡدِلُونَ

60. ወይስ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው ማን ሆነና? በእርሱም ባለ ውበት የሆኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለእናንተ ችሎታ ሳይኖራችሁ እኛ ብቻችንን አበቀልን:: ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም) ግን እነርሱ ከእውነት የሚያዘነብሉ ህዝቦች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 27

أَمَّن جَعَلَ ٱلۡأَرۡضَ قَرَارٗا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنۡهَٰرٗا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِيَ وَجَعَلَ بَيۡنَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ حَاجِزًاۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

61. ወይስ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ ለእርሷም ጋራዎችን ያደረገ በጣፋጩና በጨዋማው በሁለቱ ባህሮችም መካከል ግርዶን ያደረገ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። info
التفاسير:

external-link copy
62 : 27

أَمَّن يُجِيبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكۡشِفُ ٱلسُّوٓءَ وَيَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَآءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِيلٗا مَّا تَذَكَّرُونَ

62. ወይስ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚደርጋችሁ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሰጹም። info
التفاسير:

external-link copy
63 : 27

أَمَّن يَهۡدِيكُمۡ فِي ظُلُمَٰتِ ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ وَمَن يُرۡسِلُ ٱلرِّيَٰحَ بُشۡرَۢا بَيۡنَ يَدَيۡ رَحۡمَتِهِۦٓۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ تَعَٰلَى ٱللَّهُ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

63. ወይስ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ንፋሶችንም ከዝናቡ በፊት አብሳሪ ሆነው የሚልክ ማን ሆነና? ከአላህ ጋር ሌላ ትክክለኛ አምላክ አለን? አላህ በእርሱ ከሚያጋሯቸው ነገሮች ሁሉ ላቀ። info
التفاسير: