Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
30 : 2

وَإِذۡ قَالَ رَبُّكَ لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّي جَاعِلٞ فِي ٱلۡأَرۡضِ خَلِيفَةٗۖ قَالُوٓاْ أَتَجۡعَلُ فِيهَا مَن يُفۡسِدُ فِيهَا وَيَسۡفِكُ ٱلدِّمَآءَ وَنَحۡنُ نُسَبِّحُ بِحَمۡدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَۖ قَالَ إِنِّيٓ أَعۡلَمُ مَا لَا تَعۡلَمُونَ

30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ለመላዕክት «እኔ በምድር ላይ (ምትክ) ወኪል ላደርግ ነው።» ባለ ጊዜ (የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ)። «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ፤ የምናሞግስህ ስንሆን በምድር ውስጥ የሚያጠፉትንና ደሞችንም የሚያፈሱትን ታደርጋለህን?» አሉ:: አላህም «እኔ እናንተ የማታውቁትን ነገር ሁሉ አውቃለሁ» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 2

وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلۡأَسۡمَآءَ كُلَّهَا ثُمَّ عَرَضَهُمۡ عَلَى ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ فَقَالَ أَنۢبِـُٔونِي بِأَسۡمَآءِ هَٰٓؤُلَآءِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

31. ለአደምም ስሞችን ሁሉ አስተማረው:: ከዚያም በመላዕክት ላይ (ተሰያሚዎቹን) አቀረባቸው። «እውነተኞች ከሆናችሁ የእነዚህን ተሰያሚዎች መጠሪያ ንገሩኝ?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 2

قَالُواْ سُبۡحَٰنَكَ لَا عِلۡمَ لَنَآ إِلَّا مَا عَلَّمۡتَنَآۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ

32. እነርሱም «ጥራት ይገባህ አንተ ካስተማርከን ነገር በስተቀር እኛ ምንም እውቀት የለንም:: አንተ ብቸኛው ጥበበኛና አዋቂው ነህና›› አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 2

قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ أَنۢبِئۡهُم بِأَسۡمَآئِهِمۡۖ فَلَمَّآ أَنۢبَأَهُم بِأَسۡمَآئِهِمۡ قَالَ أَلَمۡ أَقُل لَّكُمۡ إِنِّيٓ أَعۡلَمُ غَيۡبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَأَعۡلَمُ مَا تُبۡدُونَ وَمَا كُنتُمۡ تَكۡتُمُونَ

33. አላህም «አደም ሆይ! ስሞቻቸውን ንገራቸው።» አለው። ከዚያም ስሞቻቸውን በነገራቸው ጊዜ «እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር አውቃለሁ። የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ አውቃለሁ አላልኳችሁምን?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 2

وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ أَبَىٰ وَٱسۡتَكۡبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ

34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትን «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ከዲያብሎስ በቀር መላዕክት ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ። እርሱማ እምቢ አለ። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 2

وَقُلۡنَا يَٰٓـَٔادَمُ ٱسۡكُنۡ أَنتَ وَزَوۡجُكَ ٱلۡجَنَّةَ وَكُلَا مِنۡهَا رَغَدًا حَيۡثُ شِئۡتُمَا وَلَا تَقۡرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

35. «አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ:: ግን ከበደለኞች ትሆናላችሁና ይህችን ዛፍ አትቅረቡ።» አልናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 2

فَأَزَلَّهُمَا ٱلشَّيۡطَٰنُ عَنۡهَا فَأَخۡرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيهِۖ وَقُلۡنَا ٱهۡبِطُواْ بَعۡضُكُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوّٞۖ وَلَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُسۡتَقَرّٞ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٖ

36. ሰይጣንም ከእርሷ አሳሳታቸው። ከነበሩበትም ገነት አወጣቸው። «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ሁላችሁም (ወደ ምድር) ውረዱ። ለእናንተም በምድር ላይ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አልናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 2

فَتَلَقَّىٰٓ ءَادَمُ مِن رَّبِّهِۦ كَلِمَٰتٖ فَتَابَ عَلَيۡهِۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

37. ከዚያም አደም ከጌታው የመታረቂያ ቃል ተማረ:: ጌታዉም ተማጽኖውን ተቀበለው:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና፡፡ info
التفاسير: