Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
106 : 2

۞ مَا نَنسَخۡ مِنۡ ءَايَةٍ أَوۡ نُنسِهَا نَأۡتِ بِخَيۡرٖ مِّنۡهَآ أَوۡ مِثۡلِهَآۗ أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አናቅጽ መካከል አንዱን እንኳን ብንሽር ወይም እርሱን ብናስረሳህ ከእርሱ የሚበልጥ ወይም ተመሳሳዩን እናመጣለን:: አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ መሆኑን አላወቅክምን? info
التفاسير:

external-link copy
107 : 2

أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِيّٖ وَلَا نَصِيرٍ

107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ መሆኑን እና ለእናንተም ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ ረዳት እንደሌላችሁ አላወቅክምን? info
التفاسير:

external-link copy
108 : 2

أَمۡ تُرِيدُونَ أَن تَسۡـَٔلُواْ رَسُولَكُمۡ كَمَا سُئِلَ مُوسَىٰ مِن قَبۡلُۗ وَمَن يَتَبَدَّلِ ٱلۡكُفۡرَ بِٱلۡإِيمَٰنِ فَقَدۡ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ

108. (ሰዎች ሆይ!) ከአሁን በፊት (ነብዩ) ሙሳ እንደተጠየቀው ዓይነት መልዕክተኛችሁን (ሙሐመድን) ልትጠይቁ ትፈልጋላችሁን? በእምነት ክህደትን የሚለውጥ ሁሉ በእርግጥ ትክክለኛውን መንገድ ስቷል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
109 : 2

وَدَّ كَثِيرٞ مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ لَوۡ يَرُدُّونَكُم مِّنۢ بَعۡدِ إِيمَٰنِكُمۡ كُفَّارًا حَسَدٗا مِّنۡ عِندِ أَنفُسِهِم مِّنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلۡحَقُّۖ فَٱعۡفُواْ وَٱصۡفَحُواْ حَتَّىٰ يَأۡتِيَ ٱللَّهُ بِأَمۡرِهِۦٓۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

109. ከመጽሐፍ ባለቤቶች መካከል ብዙዎቹ እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በሆነው ምቀኝነት በመገፋፋት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲያን ሊያደርጓችሁ ተመኙ:: እናም አላህ ትዕዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ይቅርታ አድርጉ:: እለፏቸዉም:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
110 : 2

وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَۚ وَمَا تُقَدِّمُواْ لِأَنفُسِكُم مِّنۡ خَيۡرٖ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ

110. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሶላትን አስተካክላችሁ ስገዱ:: ዘካንም ለተገቢዎች ስጡ:: ለነፍሶቻችሁም የምታስቀድሙትን በጎ ስራ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
111 : 2

وَقَالُواْ لَن يَدۡخُلَ ٱلۡجَنَّةَ إِلَّا مَن كَانَ هُودًا أَوۡ نَصَٰرَىٰۗ تِلۡكَ أَمَانِيُّهُمۡۗ قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

111. «ገነትን አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች የሆነ እንጂ ሌላ አይገባትም።» አሉ:: «ይህች ከንቱ ምኞታቸው ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ማስረጃችሁን አምጡ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
112 : 2

بَلَىٰۚ مَنۡ أَسۡلَمَ وَجۡهَهُۥ لِلَّهِ وَهُوَ مُحۡسِنٞ فَلَهُۥٓ أَجۡرُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦ وَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

112. ጉዳዩ እንደመሰላቸው አይደለም:: ይልቁንም በጎ ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ የሰጠ ሁሉ ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳ አለው:: በእነርሱ ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም። info
التفاسير: