Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
170 : 2

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُواْ بَلۡ نَتَّبِعُ مَآ أَلۡفَيۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَآۚ أَوَلَوۡ كَانَ ءَابَآؤُهُمۡ لَا يَعۡقِلُونَ شَيۡـٔٗا وَلَا يَهۡتَدُونَ

170. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ የለም አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር ብቻ እንከተላለን» ይላሉ:: አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና ወደ እውነት የማይመሩም ቢሆኑ ይከተሏቸዋልን? info
التفاسير:

external-link copy
171 : 2

وَمَثَلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ كَمَثَلِ ٱلَّذِي يَنۡعِقُ بِمَا لَا يَسۡمَعُ إِلَّا دُعَآءٗ وَنِدَآءٗۚ صُمُّۢ بُكۡمٌ عُمۡيٞ فَهُمۡ لَا يَعۡقِلُونَ

171. የእነዚያም በአላህ የካዱት ምሳሌ ልክ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን እንጂ ሌላን በማይሰማ እንሰሳ ላይ እንደሚጮህ (እረኛ) ብጤ ነው:: እነርሱ (እውነትን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሐቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ትክክለኛውን መንገድ የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ምንንም ነገር የሚገነዘቡ አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
172 : 2

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡ وَٱشۡكُرُواْ لِلَّهِ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ

172. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሰጠናችሁ ሲሳዮች መካከል ጥሩውን ተመገቡ:: አላህንም በብቸኝነት የምታመልኩት ከሆናችሁ እሱኑ ብቻ አመስግኑት:: info
التفاسير:

external-link copy
173 : 2

إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَيۡتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحۡمَ ٱلۡخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ بِهِۦ لِغَيۡرِ ٱللَّهِۖ فَمَنِ ٱضۡطُرَّ غَيۡرَ بَاغٖ وَلَا عَادٖ فَلَآ إِثۡمَ عَلَيۡهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ

173. (አላህ) በእናንተ ላይ እርም ያደረገባችሁ በክትን፣ ደምን፣ የአሳማ ስጋንና ከአላህ ሌላ በሆነ ስም የታረደን ስጋ ብቻ ነው:: ተገዶ ችግሩን ለማስወገድ ያክል ብቻ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይሆን (ቢመገብ) በእርሱ ላይ ምንም ሀጢአት የለበትም:: አላህ መሐሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
174 : 2

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡتُمُونَ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَيَشۡتَرُونَ بِهِۦ ثَمَنٗا قَلِيلًا أُوْلَٰٓئِكَ مَا يَأۡكُلُونَ فِي بُطُونِهِمۡ إِلَّا ٱلنَّارَ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ ٱللَّهُ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ

174. እነዚያ አላህ ካወረደው መጽሐፍ (የትኛውንም ክፍል) የሚደብቁ፤ በሱ (በደበቁትም) ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ፤ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም:: አላህም በትንሳኤ ቀን አያናግራቸዉም:: ከኃጢአትም አያጠራቸዉምም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
175 : 2

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشۡتَرَوُاْ ٱلضَّلَٰلَةَ بِٱلۡهُدَىٰ وَٱلۡعَذَابَ بِٱلۡمَغۡفِرَةِۚ فَمَآ أَصۡبَرَهُمۡ عَلَى ٱلنَّارِ

175. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት ቅጣትንም በምህረት የለወጡ ናቸው:: በእሳት ላይ ምን ታጋሽ አደረጋቸው?! info
التفاسير:

external-link copy
176 : 2

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ نَزَّلَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّۗ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخۡتَلَفُواْ فِي ٱلۡكِتَٰبِ لَفِي شِقَاقِۭ بَعِيدٖ

176. ይህም አላህ መጽሐፍን በእውነት ያወረደ በመሆኑና (በእርሱም በመካዳቸው ነው):: እነዚያም በመጽሐፉ የተለያዩት ከእውነት በራቀ ውዝግብ ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير: