แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา

หมายเลข​หน้า​:close

external-link copy
69 : 9

كَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ كَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنكُمۡ قُوَّةٗ وَأَكۡثَرَ أَمۡوَٰلٗا وَأَوۡلَٰدٗا فَٱسۡتَمۡتَعُواْ بِخَلَٰقِهِمۡ فَٱسۡتَمۡتَعۡتُم بِخَلَٰقِكُمۡ كَمَا ٱسۡتَمۡتَعَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُم بِخَلَٰقِهِمۡ وَخُضۡتُمۡ كَٱلَّذِي خَاضُوٓاْۚ أُوْلَٰٓئِكَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ

69. (አስመሳዮች ሆይ!) ተግባራችሁ ልክ እንደእነዚያ ከናንተ በፊት እንደነበሩት ህዝቦች ነው:: ከናንተ ይበልጥ በሃይል የበረቱ በገንዘብና በልጆችም ከናንተ ይበልጥ የበዙ ነበሩ:: በእድላቸው ተጠቀሙ:: እነዚያም ከእናንተ በፊት የነበሩት በዕድላቸው እንደተጠቀሙ በዕድላችሁ ተጠቀማችሁ፡፡ እንደዘባረቁትም ዘባረቃችሁ:: እነዚያ ስራዎቻቸው በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተበላሸ:: ከሳሪዎቹም ማለት እነርሱው ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
70 : 9

أَلَمۡ يَأۡتِهِمۡ نَبَأُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ قَوۡمِ نُوحٖ وَعَادٖ وَثَمُودَ وَقَوۡمِ إِبۡرَٰهِيمَ وَأَصۡحَٰبِ مَدۡيَنَ وَٱلۡمُؤۡتَفِكَٰتِۚ أَتَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظۡلِمَهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

70. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት የኑህ፤ የዓድ፤ የሰሙድ፤ የኢብራሂም ህዝቦች፤ የመድየን ባለቤቶችና የተገልባጮቹም ከተሞች ታሪክ አልመጣላቸዉምን? መልዕክተኞቻቸው ግልጽ ተዓምራትን አመጡላቸው:: አላህ የሚበድላቸው አልነበረም:: ግን በራሳቸው ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 9

وَٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتُ بَعۡضُهُمۡ أَوۡلِيَآءُ بَعۡضٖۚ يَأۡمُرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَيُطِيعُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ سَيَرۡحَمُهُمُ ٱللَّهُۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

71. ወንድ አማኞችና ሴት አማኞች ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: በደግ ነገር ያዝዛሉ:: ከክፉም ነገር ይከለክላሉ:: ሶላትን ይሰግዳሉ:: ዘካን ይሰጣሉ:: አላህንና መልዕክተኛውን ይታዘዛሉ:: እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 9

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَمَسَٰكِنَ طَيِّبَةٗ فِي جَنَّٰتِ عَدۡنٖۚ وَرِضۡوَٰنٞ مِّنَ ٱللَّهِ أَكۡبَرُۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

72. አላህ የወንድ ትክክለኛ አማኞችንና የሴት ትክክለኛ አማኞችን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል:: ከአላህ የሆነው ውዴታ ደግሞ ከሁሉ የበለጠ ነው:: ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው:: info
التفاسير: