แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา

አል ጂን

external-link copy
1 : 72

قُلۡ أُوحِيَ إِلَيَّ أَنَّهُ ٱسۡتَمَعَ نَفَرٞ مِّنَ ٱلۡجِنِّ فَقَالُوٓاْ إِنَّا سَمِعۡنَا قُرۡءَانًا عَجَبٗا

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአጋንንት የሆኑ ቡድኖች ቁርኣንን አዳመጠው እንዲህ ማለታቸው ተወረደልኝ በል: «እኛ አስደናቂ የሆነን ቁርአን ሰማን፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 72

يَهۡدِيٓ إِلَى ٱلرُّشۡدِ فَـَٔامَنَّا بِهِۦۖ وَلَن نُّشۡرِكَ بِرَبِّنَآ أَحَدٗا

2. «ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርኣን ሰማን) በእርሱም አመንን:: በጌታችን አንድንም አናጋራም:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 72

وَأَنَّهُۥ تَعَٰلَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا ٱتَّخَذَ صَٰحِبَةٗ وَلَا وَلَدٗا

3. «እነሆ የጌታችን ክብር ላቀ:: ሚስትንም ልጅንም አልያዘም:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 72

وَأَنَّهُۥ كَانَ يَقُولُ سَفِيهُنَا عَلَى ٱللَّهِ شَطَطٗا

4. «እነሆ ቂላችን በአላህ ላይ ወሰን ያለፈን ውሸት ይናገር ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 72

وَأَنَّا ظَنَنَّآ أَن لَّن تَقُولَ ٱلۡإِنسُ وَٱلۡجِنُّ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا

5. «እኛም ሰዎችና ጋኔኖች በአላህ ላይ ውሸትን ቃል አይናገሩም ማለትን ጠረጠርን» አሉ በማለት ወደእኔ ተወረደ በል። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 72

وَأَنَّهُۥ كَانَ رِجَالٞ مِّنَ ٱلۡإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٖ مِّنَ ٱلۡجِنِّ فَزَادُوهُمۡ رَهَقٗا

6. እነሆ ከሰዎች የሆኑ ወንዶች ከአጋንንት በሆኑ ወንዶች ይጠበቁ ነበር። ኩራትንም (ጥመትን) ጨመሯቸው። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 72

وَأَنَّهُمۡ ظَنُّواْ كَمَا ظَنَنتُمۡ أَن لَّن يَبۡعَثَ ٱللَّهُ أَحَدٗا

7. አላህ አንድንም አይቀሰቅስም ማለትን እንደጠረጠራችሁ እነርሱም ጠረጠሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 72

وَأَنَّا لَمَسۡنَا ٱلسَّمَآءَ فَوَجَدۡنَٰهَا مُلِئَتۡ حَرَسٗا شَدِيدٗا وَشُهُبٗا

8. እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 72

وَأَنَّا كُنَّا نَقۡعُدُ مِنۡهَا مَقَٰعِدَ لِلسَّمۡعِۖ فَمَن يَسۡتَمِعِ ٱلۡأٓنَ يَجِدۡ لَهُۥ شِهَابٗا رَّصَدٗا

9. እኛም ከእርሷ ወሬን ለማዳመጥ በመቀመጫዎች እንቀመጥ ነበር:: አሁን (ግን) የሚያዳምጥ (ሁሉ) ተጠባባቂ የእሳት ችቦ ያገኘዋል። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 72

وَأَنَّا لَا نَدۡرِيٓ أَشَرٌّ أُرِيدَ بِمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ أَرَادَ بِهِمۡ رَبُّهُمۡ رَشَدٗا

10. እኛም በምድር ውስጥ ባሉት ክፉ ተሽቷል? ወይስ በእነርሱ (በኩል) ጌታቸው ደግን ነገር ሽቷል? ማለትን አናውቅም። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 72

وَأَنَّا مِنَّا ٱلصَّٰلِحُونَ وَمِنَّا دُونَ ذَٰلِكَۖ كُنَّا طَرَآئِقَ قِدَدٗا

11. ከእኛም ውስጥ ደጋጎች አሉ:: ከእኛም ውስጥ ከዚህ ሌላ የሆኑ አሉ:: የተለያዩ መንገዶች ባለቤቶች ነበርን:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 72

وَأَنَّا ظَنَنَّآ أَن لَّن نُّعۡجِزَ ٱللَّهَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَن نُّعۡجِزَهُۥ هَرَبٗا

12. እኛም አላህን በምድር ውስጥ ፈጽሞ የማናቅተው ሸሽተንም ፈጽሞ የማናመልጠው መሆናችንን አረጋገጥን:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 72

وَأَنَّا لَمَّا سَمِعۡنَا ٱلۡهُدَىٰٓ ءَامَنَّا بِهِۦۖ فَمَن يُؤۡمِنۢ بِرَبِّهِۦ فَلَا يَخَافُ بَخۡسٗا وَلَا رَهَقٗا

13. እኛም መሪውን በሰማን ጊዜ በእርሱ አመንን:: ያ! በጌታው የሚያምን ሰው ሁሉ መጎደልንም ሆነ መጨመርን አይፈራም:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 72

وَأَنَّا مِنَّا ٱلۡمُسۡلِمُونَ وَمِنَّا ٱلۡقَٰسِطُونَۖ فَمَنۡ أَسۡلَمَ فَأُوْلَٰٓئِكَ تَحَرَّوۡاْ رَشَدٗا

14. ከእኛም ውስጥ ሙስሊሞች አሉ:: ከእኛም ውስጥ በዳዩች አሉ:: እነዚያ የሰለሙ ሰዎች ቅንን መንገድ መረጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 72

وَأَمَّا ٱلۡقَٰسِطُونَ فَكَانُواْ لِجَهَنَّمَ حَطَبٗا

15. እነዚያ በዳዩችማ ለገሀነም ማገዶ ሆኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 72

وَأَلَّوِ ٱسۡتَقَٰمُواْ عَلَى ٱلطَّرِيقَةِ لَأَسۡقَيۡنَٰهُم مَّآءً غَدَقٗا

16. (ሰዎች ሁሉ በአላህ) በመንገድ ላይ ቀጥ ባሉ ኖሮ ብዙ ዝናብን ባጠጣናቸው ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 72

لِّنَفۡتِنَهُمۡ فِيهِۚ وَمَن يُعۡرِضۡ عَن ذِكۡرِ رَبِّهِۦ يَسۡلُكۡهُ عَذَابٗا صَعَدٗا

17. በእርሱ ልንፈትናቸው (ባጠጣናቸው ነበር)። ያ ጌታውን ከማስታወስ የሚያፈገፍግ ሰው አስቸጋሪ ቅጣት ውስጥ ያስገባዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 72

وَأَنَّ ٱلۡمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدۡعُواْ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدٗا

18. መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው:: እናም በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ማለትን ተወረደልኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 72

وَأَنَّهُۥ لَمَّا قَامَ عَبۡدُ ٱللَّهِ يَدۡعُوهُ كَادُواْ يَكُونُونَ عَلَيۡهِ لِبَدٗا

19. እነሆ የአላህ ባሪያ (ሙሐመድ) አላህን የሚጠራው ሆኖ በተነሳ ጊዜ ጋኒኖቹ በእርሱ ላይ ድርብርቦች ሊሆኑ ቀረቡ:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 72

قُلۡ إِنَّمَآ أَدۡعُواْ رَبِّي وَلَآ أُشۡرِكُ بِهِۦٓ أَحَدٗا

20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ የማመልከው ጌታየን ብቻ ነው:: በእርሱ አንድንም አላጋራም» በል። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 72

قُلۡ إِنِّي لَآ أَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرّٗا وَلَا رَشَدٗا

21. «እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ሆነ ማቅናትን አልችልም» በል። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 72

قُلۡ إِنِّي لَن يُجِيرَنِي مِنَ ٱللَّهِ أَحَدٞ وَلَنۡ أَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلۡتَحَدًا

22. «እኔን ከአላህ ቅጣት አንድም (አካል) አያድነኝም:: ከእርሱ ሌላ መጠጊያም አላገኝም» በል። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 72

إِلَّا بَلَٰغٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِسَٰلَٰتِهِۦۚ وَمَن يَعۡصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَإِنَّ لَهُۥ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا

23. ከአላህ የሆኑ መልዕክቶችን ከማድረስ በስተቀር አልችልም:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚያምጽ ሁሉ ለእርሱ የገሀነም እሳት አለው:: በውስጧም ዘላለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 72

حَتَّىٰٓ إِذَا رَأَوۡاْ مَا يُوعَدُونَ فَسَيَعۡلَمُونَ مَنۡ أَضۡعَفُ نَاصِرٗا وَأَقَلُّ عَدَدٗا

24. የሚስፈራሩበትንም ባዩ ጊዜ ረዳተ ደካማ ቁጥሩም አነስተኛ የሆነው ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 72

قُلۡ إِنۡ أَدۡرِيٓ أَقَرِيبٞ مَّا تُوعَدُونَ أَمۡ يَجۡعَلُ لَهُۥ رَبِّيٓ أَمَدًا

25. «ያ! የምትስፈራሩበት ነገር ቅርብ ወይም ጌታየ ለእርሱ የተወሰነ ጊዜን የሚያደርግለት እሩቅ መሆኑን አላውቅም።» በላቸው info
التفاسير:

external-link copy
26 : 72

عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ فَلَا يُظۡهِرُ عَلَىٰ غَيۡبِهِۦٓ أَحَدًا

26. እርሱም እሩቁን ሚስጢር አዋቂ ነው::በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
27 : 72

إِلَّا مَنِ ٱرۡتَضَىٰ مِن رَّسُولٖ فَإِنَّهُۥ يَسۡلُكُ مِنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَمِنۡ خَلۡفِهِۦ رَصَدٗا

27. (በሚስጢሩም ላይ) ከመልዕክተኛው ለወደደው ቢሆን እንጂ (ለሌላ አንድንም አያሳውቅም):: አይገልጽም:: ለእርሱም ከበስተፊቱም ከበስተኋላዉም ጠባቂዎቸን ያደርግለታል:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 72

لِّيَعۡلَمَ أَن قَدۡ أَبۡلَغُواْ رِسَٰلَٰتِ رَبِّهِمۡ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيۡهِمۡ وَأَحۡصَىٰ كُلَّ شَيۡءٍ عَدَدَۢا

28. ከእነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀት የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲሆን የጌታቸውን መልዕክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ (ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል):: info
التفاسير: