แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา

ቃፍ

external-link copy
1 : 50

قٓۚ وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡمَجِيدِ

1. ቃፍ ፤ በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 50

بَلۡ عَجِبُوٓاْ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٞ مِّنۡهُمۡ فَقَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا شَيۡءٌ عَجِيبٌ

2. ይልቁንም ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለ መጣላቸው ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ አስደናቂ ነገር ነው። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 50

أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗاۖ ذَٰلِكَ رَجۡعُۢ بَعِيدٞ

3. «በሞትንና አፈር በሆንን ጊዜ እንመለሳለንን? ይህ ሩቅ የሆነ መመለስ ነው።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 50

قَدۡ عَلِمۡنَا مَا تَنقُصُ ٱلۡأَرۡضُ مِنۡهُمۡۖ وَعِندَنَا كِتَٰبٌ حَفِيظُۢ

4. ከእነርሱ አካል ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ አውቀናል:: እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 50

بَلۡ كَذَّبُواْ بِٱلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَهُمۡ فَهُمۡ فِيٓ أَمۡرٖ مَّرِيجٍ

5. ይልቁንም ቁርኣን በመጣላቸው ጊዜ አስተባበሉ። እነርሱም በተምታታ ነገር ውስጥ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 50

أَفَلَمۡ يَنظُرُوٓاْ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَوۡقَهُمۡ كَيۡفَ بَنَيۡنَٰهَا وَزَيَّنَّٰهَا وَمَا لَهَا مِن فُرُوجٖ

6. ወደ ሰማይም ከበላያቸው ስትሆን ለእርሷ ምንም ቀዳዳዎች የሌሏቸው ሆነው እንዴት እንደገነባናትና በከዋክብት እንዳጌጥናት አልተመለከቱምን? info
التفاسير:

external-link copy
7 : 50

وَٱلۡأَرۡضَ مَدَدۡنَٰهَا وَأَلۡقَيۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ وَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجِۭ بَهِيجٖ

7. ምድርም ዘረጋናት በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት :: በውስጧም ከሚያስደስት አይነት ሁሉ አበቀልን:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 50

تَبۡصِرَةٗ وَذِكۡرَىٰ لِكُلِّ عَبۡدٖ مُّنِيبٖ

8. ይህንን ያደረግነው ተመላሽ ለሆነ ባሪያ ሁሉ ለማሳየትና ለማስገንዘብ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 50

وَنَزَّلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ مُّبَٰرَكٗا فَأَنۢبَتۡنَا بِهِۦ جَنَّٰتٖ وَحَبَّ ٱلۡحَصِيدِ

9. ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን አዝመራ ፍሬ አበቀልን:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 50

وَٱلنَّخۡلَ بَاسِقَٰتٖ لَّهَا طَلۡعٞ نَّضِيدٞ

10. ዘንባባንም ረዣዥም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትሆን አበቀልን:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 50

رِّزۡقٗا لِّلۡعِبَادِۖ وَأَحۡيَيۡنَا بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗاۚ كَذَٰلِكَ ٱلۡخُرُوجُ

11. ለባሮቹ ሲሳይ ትሆን ዘንድ (አዘጋጀናት):: በእርሱም የሞተችን ሀገር ሕያው አደረግንበት:: ከመቃብር መውጣትም ልክ እንደዚሁ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 50

كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَأَصۡحَٰبُ ٱلرَّسِّ وَثَمُودُ

12. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦችና የረስስ ሰዎችም ሰሙድም አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 50

وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ وَإِخۡوَٰنُ لُوطٖ

13. ዓድም ፈርዖንም የሉጥ ወንድሞችም፤ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 50

وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡأَيۡكَةِ وَقَوۡمُ تُبَّعٖۚ كُلّٞ كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ وَعِيدِ

14. የጫካው ባለቤቶችም የቱብበዕ ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኞችን አስተባበሉ:: ዛቻየም ተረጋገጠባቸው። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 50

أَفَعَيِينَا بِٱلۡخَلۡقِ ٱلۡأَوَّلِۚ بَلۡ هُمۡ فِي لَبۡسٖ مِّنۡ خَلۡقٖ جَدِيدٖ

15. በመጀመሪያው መፍጠር ደከምን? በእውነቱ እነርሱ ከአዲስ መፍጠር በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير: