แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา

หมายเลข​หน้า​:close

external-link copy
34 : 43

وَلِبُيُوتِهِمۡ أَبۡوَٰبٗا وَسُرُرًا عَلَيۡهَا يَتَّكِـُٔونَ

34. ለቤቶቻቸው የብር በሮች፤ ለሚደገፉባቸዉም የብር አልጋዎች፤(ባደረግንላቸው ነበር)። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 43

وَزُخۡرُفٗاۚ وَإِن كُلُّ ذَٰلِكَ لَمَّا مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَٱلۡأٓخِرَةُ عِندَ رَبِّكَ لِلۡمُتَّقِينَ

35. የወርቅ ጌጥንም ባደረግንላቸው ነበር። ይህም ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጣቀሚያ እንጂ ሌላ አይደለም:: ጠፊ ነው:: መጨረሻይቱም አገር በጌታህ ዘንድ ለጥንቁቆች ብቻ ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 43

وَمَن يَعۡشُ عَن ذِكۡرِ ٱلرَّحۡمَٰنِ نُقَيِّضۡ لَهُۥ شَيۡطَٰنٗا فَهُوَ لَهُۥ قَرِينٞ

36. (በቁርኣን ከተወሳው) ከአል-ረሕማን ግሳጼ የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን። ስለዚህ እርሱ ለእርሱ የሁልግዜ ቁራኛው ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 43

وَإِنَّهُمۡ لَيَصُدُّونَهُمۡ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَيَحۡسَبُونَ أَنَّهُم مُّهۡتَدُونَ

37. እነርሱም (ተደናባሪዎቹ) ሁሉ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመሪዎች መሆናቸውን የሚያስቡ ሲሆኑ እነርሱ (ሰይጣናት) ከቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ያግዷቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 43

حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَنَا قَالَ يَٰلَيۡتَ بَيۡنِي وَبَيۡنَكَ بُعۡدَ ٱلۡمَشۡرِقَيۡنِ فَبِئۡسَ ٱلۡقَرِينُ

38. (በትንሳኤ) ወደ እኛ በመጣ ጊዜ «(ቁራኛዬ ሆይ) በእኔና ባንተ መካከል የምስራቅና የምዕራብ ርቀት በኖረ ዋ ምኞቴ! ምን የከፋ ቁራኛ ነህ።» ይላል:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 43

وَلَن يَنفَعَكُمُ ٱلۡيَوۡمَ إِذ ظَّلَمۡتُمۡ أَنَّكُمۡ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ

39. (ከሓዲያን ሆይ!) ስለ በደላችሁም ዛሬ እናንተ በቅጣት ተጋሪዎች መሆናችሁ አይጠቅማችሁም (ይባላሉ)። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 43

أَفَأَنتَ تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ أَوۡ تَهۡدِي ٱلۡعُمۡيَ وَمَن كَانَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ደንቆሮዎችን ታሰማለህን? ወይስ እውሮችንና በግልጽ ጥመት ውስጥ የሆኑ ሰዎችን ትመራለህን? info
التفاسير:

external-link copy
41 : 43

فَإِمَّا نَذۡهَبَنَّ بِكَ فَإِنَّا مِنۡهُم مُّنتَقِمُونَ

41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቅጣታቸውን ሳታይ ብንወስድህ እኛ ከእነርሱ ተበቃዮች ነን። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 43

أَوۡ نُرِيَنَّكَ ٱلَّذِي وَعَدۡنَٰهُمۡ فَإِنَّا عَلَيۡهِم مُّقۡتَدِرُونَ

42. ወይም ያንን የቀጠርናቸውን ብናሳይህ እኛ በእነርሱ ቅጣት ላይ ቻይዎች ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 43

فَٱسۡتَمۡسِكۡ بِٱلَّذِيٓ أُوحِيَ إِلَيۡكَۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ:: አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 43

وَإِنَّهُۥ لَذِكۡرٞ لَّكَ وَلِقَوۡمِكَۖ وَسَوۡفَ تُسۡـَٔلُونَ

44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ (ቁርኣን) ላንተም ሆነ ለህዝቦችህ ታላቅ ክብር ነው:: ወደፊተም ከርሱ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 43

وَسۡـَٔلۡ مَنۡ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رُّسُلِنَآ أَجَعَلۡنَا مِن دُونِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ءَالِهَةٗ يُعۡبَدُونَ

45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞችም ካንተ በፊት የላክናቸው ከአር-ረሕማን ሌላ የሚገዙዋቸው የሆነን አማልክት አድርገን እንደሆነ (ተከታዮቻቸውን) ጠይቃቸው። info
التفاسير:

external-link copy
46 : 43

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَقَالَ إِنِّي رَسُولُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም በተዓምራታችን ወደ ፈርዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን:: «እኔ የዓለማቱ ጌታ መልዕክተኛ ነኝ» አላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 43

فَلَمَّا جَآءَهُم بِـَٔايَٰتِنَآ إِذَا هُم مِّنۡهَا يَضۡحَكُونَ

47. በተዓምራታችን በመጣላቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ በእርሷ ይስቃሉ:: info
التفاسير: