แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา

หมายเลข​หน้า​:close

external-link copy
15 : 34

لَقَدۡ كَانَ لِسَبَإٖ فِي مَسۡكَنِهِمۡ ءَايَةٞۖ جَنَّتَانِ عَن يَمِينٖ وَشِمَالٖۖ كُلُواْ مِن رِّزۡقِ رَبِّكُمۡ وَٱشۡكُرُواْ لَهُۥۚ بَلۡدَةٞ طَيِّبَةٞ وَرَبٌّ غَفُورٞ

15. ለሰበእ ነገዶች በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው:: ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች ነበሯቸው:: «ከጌታችሁ ሲሳይ ብሉ ለእሱም አመስግኑ:: አገራችሁ ውብ አገር ናት:: ጌታችሁም መሃሪ ጌታ ነው» ተባሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 34

فَأَعۡرَضُواْ فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ سَيۡلَ ٱلۡعَرِمِ وَبَدَّلۡنَٰهُم بِجَنَّتَيۡهِمۡ جَنَّتَيۡنِ ذَوَاتَيۡ أُكُلٍ خَمۡطٖ وَأَثۡلٖ وَشَيۡءٖ مِّن سِدۡرٖ قَلِيلٖ

16. አላህን ከማመስገን ዞሩም:: በእነርሱም ላይ የግድቡን ጎርፍ ለቀቅንባቸው:: በሁለቱ አትክልቶቻቸዉም ሌሎች ሁለትን አትክልቶች ባለ መርጋጋ ፍሬዎችን ባለ ጠደቻና ከቁርቁራም ባለ ጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 34

ذَٰلِكَ جَزَيۡنَٰهُم بِمَا كَفَرُواْۖ وَهَلۡ نُجَٰزِيٓ إِلَّا ٱلۡكَفُورَ

17. በመካዳቸው ምክንያት ይህንን መነዳናቸው:: (እንደዚህ ያለውን ቅጣት) በጣም ከሓዲ ለሆነ ሰው ብቻ እንጂ ለሌላው እንሰጣለን? info
التفاسير:

external-link copy
18 : 34

وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُمۡ وَبَيۡنَ ٱلۡقُرَى ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَا قُرٗى ظَٰهِرَةٗ وَقَدَّرۡنَا فِيهَا ٱلسَّيۡرَۖ سِيرُواْ فِيهَا لَيَالِيَ وَأَيَّامًا ءَامِنِينَ

18. በእነርሱና በዚያች በውስጧ በረከትን ባደረግንባት አገር (በሻም) መካከልም ተከታታይ መንደሮችን (ቅጥልጥል ከተሞች) አደረግን:: በእርሷም ጉዞን ወሰንን። «በሌሊቶችም ሆነ በቀኖች ዉስጥ ጸጥተኞች ሆናችሁ ተጓዙ» (አልን):: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 34

فَقَالُواْ رَبَّنَا بَٰعِدۡ بَيۡنَ أَسۡفَارِنَا وَظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَحَادِيثَ وَمَزَّقۡنَٰهُمۡ كُلَّ مُمَزَّقٍۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّكُلِّ صَبَّارٖ شَكُورٖ

19. «ጌታችን ሆይ! በጉዞዎቻችን መካከል አራርቅልን» አሉም:: ነፍሶቻቸውንም በደሉ:: መገረሚያ ወሬዎችም አደረግናቸው:: መበታተንንም ሁሉ በታተንናቸው:: በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ ብዙ መገለጫዎች አሉበት:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 34

وَلَقَدۡ صَدَّقَ عَلَيۡهِمۡ إِبۡلِيسُ ظَنَّهُۥ فَٱتَّبَعُوهُ إِلَّا فَرِيقٗا مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

20. ዲያብሎስም በእነርሱ ላይ ምኞቱን በእርግጥ ፈጸመ:: እናም ከአመኑት የሆኑት ቡድኖች በስተቀር ተከተሉት:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 34

وَمَا كَانَ لَهُۥ عَلَيۡهِم مِّن سُلۡطَٰنٍ إِلَّا لِنَعۡلَمَ مَن يُؤۡمِنُ بِٱلۡأٓخِرَةِ مِمَّنۡ هُوَ مِنۡهَا فِي شَكّٖۗ وَرَبُّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ حَفِيظٞ

21. በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያምነውን ከዚያ እርሱ ከእርሷ በመጠራጠር ውስጥ ከሆነው ሰው ለይተን እንድናውቅ እንጂ በእነርሱ ላይ ለእርሱ ምንም ስልጣን አልነበረዉም:: ጌታህም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 34

قُلِ ٱدۡعُواْ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمۡلِكُونَ مِثۡقَالَ ذَرَّةٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا لَهُمۡ فِيهِمَا مِن شِرۡكٖ وَمَا لَهُۥ مِنۡهُم مِّن ظَهِيرٖ

22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ አማልክት ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥሩ:: በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ የብናኝ ክብደት ያህል እንኳ ምንም አይችሉም:: ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸዉም:: ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለዉም።» በላቸው:: info
التفاسير: