แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา

หมายเลข​หน้า​:close

external-link copy
197 : 2

ٱلۡحَجُّ أَشۡهُرٞ مَّعۡلُومَٰتٞۚ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ ٱلۡحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي ٱلۡحَجِّۗ وَمَا تَفۡعَلُواْ مِنۡ خَيۡرٖ يَعۡلَمۡهُ ٱللَّهُۗ وَتَزَوَّدُواْ فَإِنَّ خَيۡرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُونِ يَٰٓأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ

197. ሐጅ የሚፈጸመው በተወሰኑ የታወቁ ወራት ነው:: እናም በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ግዴታ የገባ ሰው በሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት፤ በአላህ ላይ ማመጽና ክርክር አያደርግም:: (ሙስሊሞች ሆይ!)የምትሰሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል። ስንቅም ያዙ:: ከስንቅ ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው:: የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! እኔን ብቻ ፍሩኝ። info
التفاسير:

external-link copy
198 : 2

لَيۡسَ عَلَيۡكُمۡ جُنَاحٌ أَن تَبۡتَغُواْ فَضۡلٗا مِّن رَّبِّكُمۡۚ فَإِذَآ أَفَضۡتُم مِّنۡ عَرَفَٰتٖ فَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ عِندَ ٱلۡمَشۡعَرِ ٱلۡحَرَامِۖ وَٱذۡكُرُوهُ كَمَا هَدَىٰكُمۡ وَإِن كُنتُم مِّن قَبۡلِهِۦ لَمِنَ ٱلضَّآلِّينَ

198. በሐጅ ጊዜ (በስራ) ከጌታችሁ ችሮታን በመፈለጋችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ከአረፋት በተንቀሳቀሳችሁም ጊዜ መሸዐረል ሀራም ዘንድ ስትደርሱ አላህን አውሱ:: ወደ ቀናው የኢስላም መንገድ ስለመራችሁም አውሱት:: ቀደም ሲል በእርግጥ ከተሳሳቾች ነበራችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
199 : 2

ثُمَّ أَفِيضُواْ مِنۡ حَيۡثُ أَفَاضَ ٱلنَّاسُ وَٱسۡتَغۡفِرُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

199. ከዚያ ሰዎች ከተንቀሳቀሱበት ስፍራ ተንቀሳቀሱ :: የአላህንም ምህረት ለምኑ:: አላህ በእጅጉ መሀሪና አዛኝ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
200 : 2

فَإِذَا قَضَيۡتُم مَّنَٰسِكَكُمۡ فَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَذِكۡرِكُمۡ ءَابَآءَكُمۡ أَوۡ أَشَدَّ ذِكۡرٗاۗ فَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ رَبَّنَآ ءَاتِنَا فِي ٱلدُّنۡيَا وَمَا لَهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنۡ خَلَٰقٖ

200. የሐጅ ስራዎቻችሁን በፈጸማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ከእርሱም ይበልጥ በበረታ አላህን አውሱ:: ከሰዎችም መካከል፡- «ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም መልካም እድልን ስጠን።» የሚል ሰው አለ:: ለእርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
201 : 2

وَمِنۡهُم مَّن يَقُولُ رَبَّنَآ ءَاتِنَا فِي ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٗ وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِ حَسَنَةٗ وَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ

201. ከእነርሱም መካከል «ጌታችን ሆይ! በምድር ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን:: ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
202 : 2

أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ نَصِيبٞ مِّمَّا كَسَبُواْۚ وَٱللَّهُ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ

202. እነዚያ ከሰሩት በጎ ስራ ድርሻ አላቸው:: አላህም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ info
التفاسير: