แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - โดยอะคาเดมีแอฟริกา

หมายเลข​หน้า​:close

external-link copy
46 : 11

قَالَ يَٰنُوحُ إِنَّهُۥ لَيۡسَ مِنۡ أَهۡلِكَۖ إِنَّهُۥ عَمَلٌ غَيۡرُ صَٰلِحٖۖ فَلَا تَسۡـَٔلۡنِ مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٌۖ إِنِّيٓ أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ

46. አላህም «ኑህ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም:: እርሱ መልካም ያልሆነ ስራ ነው:: በእርሱ እውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ:: እኔ ከአላዋቂዎች እንዳትሆን እገስጽሃለሁ።» አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 11

قَالَ رَبِّ إِنِّيٓ أَعُوذُ بِكَ أَنۡ أَسۡـَٔلَكَ مَا لَيۡسَ لِي بِهِۦ عِلۡمٞۖ وَإِلَّا تَغۡفِرۡ لِي وَتَرۡحَمۡنِيٓ أَكُن مِّنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

47. «ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ እውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ:: ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 11

قِيلَ يَٰنُوحُ ٱهۡبِطۡ بِسَلَٰمٖ مِّنَّا وَبَرَكَٰتٍ عَلَيۡكَ وَعَلَىٰٓ أُمَمٖ مِّمَّن مَّعَكَۚ وَأُمَمٞ سَنُمَتِّعُهُمۡ ثُمَّ يَمَسُّهُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٞ

48. «ኑህ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ህዝቦች ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ወደ ምድር ውረድ:: ከነሱው ዘሮች የሆኑ ህዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን:: ከዚያም ከእኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይደርስባቸዋል።» ተባለ። info
التفاسير:

external-link copy
49 : 11

تِلۡكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡغَيۡبِ نُوحِيهَآ إِلَيۡكَۖ مَا كُنتَ تَعۡلَمُهَآ أَنتَ وَلَا قَوۡمُكَ مِن قَبۡلِ هَٰذَاۖ فَٱصۡبِرۡۖ إِنَّ ٱلۡعَٰقِبَةَ لِلۡمُتَّقِينَ

49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ዘገባ ከሩቁ ወሬዎች መካከል ወደ አንተ ያወረድነው ነው:: አንተም ሆንክ ህዝቦችህ ከዚህ በፊት የምታውቁት አልነበራችሁም:: ታገሥ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ብቻ ናትና:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 11

وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمۡ هُودٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۖ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا مُفۡتَرُونَ

50. ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን:: አላቸው፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እናንተ ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 11

يَٰقَوۡمِ لَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ أَجۡرًاۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱلَّذِي فَطَرَنِيٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

51. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይም ምንዳን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ በዚያ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም:: አታውቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
52 : 11

وَيَٰقَوۡمِ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِ يُرۡسِلِ ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡكُم مِّدۡرَارٗا وَيَزِدۡكُمۡ قُوَّةً إِلَىٰ قُوَّتِكُمۡ وَلَا تَتَوَلَّوۡاْ مُجۡرِمِينَ

52. «ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተጸጸቱ:: ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና:: ወደ ኃይላችሁም ሀይልን ይጨምርላችኋል:: አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ::» info
التفاسير:

external-link copy
53 : 11

قَالُواْ يَٰهُودُ مَا جِئۡتَنَا بِبَيِّنَةٖ وَمَا نَحۡنُ بِتَارِكِيٓ ءَالِهَتِنَا عَن قَوۡلِكَ وَمَا نَحۡنُ لَكَ بِمُؤۡمِنِينَ

53. እነርሱም አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጂ አልመጣህልንም:: እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም:: እኛም ላንተ ትክክለኛ አማኞች አይደለንም። info
التفاسير: