แปล​ความหมาย​อัลกุรอาน​ - คำแปลภาษาอัมฮารา - มุฮัมมัด ศอดิก

หมายเลข​หน้า​:close

external-link copy
53 : 12

۞ وَمَآ أُبَرِّئُ نَفۡسِيٓۚ إِنَّ ٱلنَّفۡسَ لَأَمَّارَةُۢ بِٱلسُّوٓءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّيٓۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٞ رَّحِيمٞ

«ነፍሴንም (ከስሕተት) አላጠራም፡፡ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ ያዘነላት (የጠበቃት) ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» (አለ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
54 : 12

وَقَالَ ٱلۡمَلِكُ ٱئۡتُونِي بِهِۦٓ أَسۡتَخۡلِصۡهُ لِنَفۡسِيۖ فَلَمَّا كَلَّمَهُۥ قَالَ إِنَّكَ ٱلۡيَوۡمَ لَدَيۡنَا مَكِينٌ أَمِينٞ

ንጉሡም «እርሱን አምጡልኝ ለራሴ ግለኛ አደርገዋለሁና» አለ፡፡ ባናገረውም ጊዜ «አንተ ዛሬ እኛ ዘንድ ባለሟል ታማኝ ነህ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 12

قَالَ ٱجۡعَلۡنِي عَلَىٰ خَزَآئِنِ ٱلۡأَرۡضِۖ إِنِّي حَفِيظٌ عَلِيمٞ

«በምድር ግምጃ ቤቶች ላይ (ሹም) አድርገኝ፡፡ እኔ ጠባቂ አዋቂ ነኝና» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 12

وَكَذَٰلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَتَبَوَّأُ مِنۡهَا حَيۡثُ يَشَآءُۚ نُصِيبُ بِرَحۡمَتِنَا مَن نَّشَآءُۖ وَلَا نُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ

እንደዚሁም ለዩሱፍ በምድር ላይ ከእርሷ በፈለገው ስፍራ የሚሰፍር ሲሆን አስመቸነው፡፡ በችሮታችን የምንሻውን ሰው እንለያለን፡፡ የበጎ ሠሪዎችንም ዋጋ አናጠፋም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 12

وَلَأَجۡرُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٞ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ

የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ለእነዚያ ላመኑትና ይጠነቀቁ ለነበሩት የበለጠ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 12

وَجَآءَ إِخۡوَةُ يُوسُفَ فَدَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَعَرَفَهُمۡ وَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ

የዩሱፍ ወንድሞችም መጡ፡፡ በእርሱም ላይ ገቡ፡፡ እነሱም እርሱን የሳቱት ሲሆኑ ዐወቃቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 12

وَلَمَّا جَهَّزَهُم بِجَهَازِهِمۡ قَالَ ٱئۡتُونِي بِأَخٖ لَّكُم مِّنۡ أَبِيكُمۡۚ أَلَا تَرَوۡنَ أَنِّيٓ أُوفِي ٱلۡكَيۡلَ وَأَنَا۠ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ

(ጉዳያቸውን ፈጽሞ) ስንቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ አለ፡- «ከአባታችሁ በኩል የሆነውን ወንድማችሁን አምጡልኝ፡፡ እኔ ከአስተናጋጆች ሁሉ በላጭ ስሆን፤ ስፍርን የምሞላ መሆኔን አታዩምን info
التفاسير:

external-link copy
60 : 12

فَإِن لَّمۡ تَأۡتُونِي بِهِۦ فَلَا كَيۡلَ لَكُمۡ عِندِي وَلَا تَقۡرَبُونِ

እርሱንም ባታመጡልኝ እኔ ዘንድ ለእናንተ ስፍር የላችሁም፤ አትቀርቡኝምም፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
61 : 12

قَالُواْ سَنُرَٰوِدُ عَنۡهُ أَبَاهُ وَإِنَّا لَفَٰعِلُونَ

«ስለእርሱ አባቱን በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡ እኛም (ይህንን) በእርግጥ ሠሪዎች ነን» አሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
62 : 12

وَقَالَ لِفِتۡيَٰنِهِ ٱجۡعَلُواْ بِضَٰعَتَهُمۡ فِي رِحَالِهِمۡ لَعَلَّهُمۡ يَعۡرِفُونَهَآ إِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمۡ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ

ለአሽከሮቹም «ሸቀጣቸውን (ገንዘባቸውን) ወደ ቤተሰቦቻቸው በተመለሱ ጊዜ ያውቋት ዘንድ በየጓዞቻቸው ውስጥ አድርጉላቸው፡፡ ሊመለሱ ይከጀላልና» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
63 : 12

فَلَمَّا رَجَعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيهِمۡ قَالُواْ يَٰٓأَبَانَا مُنِعَ مِنَّا ٱلۡكَيۡلُ فَأَرۡسِلۡ مَعَنَآ أَخَانَا نَكۡتَلۡ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ

ወደ አባታቸውም በተመሰሉ ጊዜ፡- «አባታችን ሆይ! (ወንድማችንን እስከምንወስድ) ስፍር ከእኛ ተከልክሏል፡፡ ስለዚህ ወንድማችንን ከእኛ ጋር ላከው፡፡ ይሰፍርልናልና እኛም ለርሱ ጠባቂዎች ነን» አሉ፡፡ info
التفاسير: