அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - முஹம்மத் சாதிக்

பக்க எண்:close

external-link copy
59 : 24

وَإِذَا بَلَغَ ٱلۡأَطۡفَٰلُ مِنكُمُ ٱلۡحُلُمَ فَلۡيَسۡتَـٔۡذِنُواْ كَمَا ٱسۡتَـٔۡذَنَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمۡ ءَايَٰتِهِۦۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ

ከእናንተም ሕፃናቶቹ አቅመ አዳምን በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት (ታላላቆቹ) እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
60 : 24

وَٱلۡقَوَٰعِدُ مِنَ ٱلنِّسَآءِ ٱلَّٰتِي لَا يَرۡجُونَ نِكَاحٗا فَلَيۡسَ عَلَيۡهِنَّ جُنَاحٌ أَن يَضَعۡنَ ثِيَابَهُنَّ غَيۡرَ مُتَبَرِّجَٰتِۭ بِزِينَةٖۖ وَأَن يَسۡتَعۡفِفۡنَ خَيۡرٞ لَّهُنَّۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٞ

ከሴቶችም እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ተቀማጮች (ባልቴቶች)፤ በጌጥ የተገለፁ ሳይኾኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡ ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
61 : 24

لَّيۡسَ عَلَى ٱلۡأَعۡمَىٰ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡأَعۡرَجِ حَرَجٞ وَلَا عَلَى ٱلۡمَرِيضِ حَرَجٞ وَلَا عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمۡ أَن تَأۡكُلُواْ مِنۢ بُيُوتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ ءَابَآئِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أُمَّهَٰتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ إِخۡوَٰنِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أَخَوَٰتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أَعۡمَٰمِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ عَمَّٰتِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ أَخۡوَٰلِكُمۡ أَوۡ بُيُوتِ خَٰلَٰتِكُمۡ أَوۡ مَا مَلَكۡتُم مَّفَاتِحَهُۥٓ أَوۡ صَدِيقِكُمۡۚ لَيۡسَ عَلَيۡكُمۡ جُنَاحٌ أَن تَأۡكُلُواْ جَمِيعًا أَوۡ أَشۡتَاتٗاۚ فَإِذَا دَخَلۡتُم بُيُوتٗا فَسَلِّمُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمۡ تَحِيَّةٗ مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِ مُبَٰرَكَةٗ طَيِّبَةٗۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ

(ከሰዎች ጋር በመብላት) በዕውር ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በአንካሳም ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በበሽተኛም ላይ ኀጢአት የለበትም፡፡ በነፍሶቻችሁም ላይ ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከወንድሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከእኅቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአጎቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከአክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከየሹሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከየሹሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎቹን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት (ብትበሉ) ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ተሰብስባችሁ ወይም ተለያይታችሁ ብትበሉ በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ፤ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ፡፡ እንደዚሁ አላህ አንቀጾችን ለእናንተ ያብራራል፡፡ ልታውቁ ይከጀላልና፡፡ info
التفاسير: