அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - முஹம்மத் சாதிக்

பக்க எண்:close

external-link copy
11 : 24

إِنَّ ٱلَّذِينَ جَآءُو بِٱلۡإِفۡكِ عُصۡبَةٞ مِّنكُمۡۚ لَا تَحۡسَبُوهُ شَرّٗا لَّكُمۖ بَلۡ هُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۚ لِكُلِّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُم مَّا ٱكۡتَسَبَ مِنَ ٱلۡإِثۡمِۚ وَٱلَّذِي تَوَلَّىٰ كِبۡرَهُۥ مِنۡهُمۡ لَهُۥ عَذَابٌ عَظِيمٞ

እነዚያ መጥፎን ውሸት ያመጡ ከናንተው የኾኑ ጭፍሮች ናቸው፡፡ ለእናንተ ክፉ ነገር እንደሆነ አታስቡት። በእውነቱ እሱ ለናንተ መልካም ነገር ነው። ከእነሱ ለእያንዳዱ ሰው ከሃጥአት የሰራው ስራ ዋጋ አለው። ያም ከነሱ ትልቁን ሃጥአት የተሸከመው ለርሱ ከባድ ቅጣት አለው። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 24

لَّوۡلَآ إِذۡ سَمِعۡتُمُوهُ ظَنَّ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتُ بِأَنفُسِهِمۡ خَيۡرٗا وَقَالُواْ هَٰذَآ إِفۡكٞ مُّبِينٞ

(ውሸቱን) በሰማችሁት ጊዜ ምእምናንና ምእምናት በጎሶቻቸው ለምን ደግን ነገር አልጠረጠሩም ለምንስ ይህ ግልጽ ውሸት ነው አላሉም? info
التفاسير:

external-link copy
13 : 24

لَّوۡلَا جَآءُو عَلَيۡهِ بِأَرۡبَعَةِ شُهَدَآءَۚ فَإِذۡ لَمۡ يَأۡتُواْ بِٱلشُّهَدَآءِ فَأُوْلَٰٓئِكَ عِندَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلۡكَٰذِبُونَ

በእርሱ ላይ ለምን አራትን ምስክሮች አላመጡም ምስክሮቹንም ካላመጡ እነዚያ አላህ ዘንድ ውሸታሞቹ እነሱ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 24

وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ لَمَسَّكُمۡ فِي مَآ أَفَضۡتُمۡ فِيهِ عَذَابٌ عَظِيمٌ

በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም በእናንተ ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በውስጡ በገባችሁበት ወሬ ምክንያት ታላቅ ቅጣት በእርግጥ በደረሰባችሁ ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 24

إِذۡ تَلَقَّوۡنَهُۥ بِأَلۡسِنَتِكُمۡ وَتَقُولُونَ بِأَفۡوَاهِكُم مَّا لَيۡسَ لَكُم بِهِۦ عِلۡمٞ وَتَحۡسَبُونَهُۥ هَيِّنٗا وَهُوَ عِندَ ٱللَّهِ عَظِيمٞ

በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ (ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 24

وَلَوۡلَآ إِذۡ سَمِعۡتُمُوهُ قُلۡتُم مَّا يَكُونُ لَنَآ أَن نَّتَكَلَّمَ بِهَٰذَا سُبۡحَٰنَكَ هَٰذَا بُهۡتَٰنٌ عَظِيمٞ

በሰማችሁትም ጊዜ በዚህ ልንናገር ለእኛ አይገባንም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው፤ አትሉም ነበርን? info
التفاسير:

external-link copy
17 : 24

يَعِظُكُمُ ٱللَّهُ أَن تَعُودُواْ لِمِثۡلِهِۦٓ أَبَدًا إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

ምእመናን እንደኾናችሁ ወደ ብጤው በፍፁም እንዳትመለሱ አላህ ይገስጻችኋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 24

وَيُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِۚ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

ለእናንተም አላህ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 24

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحِبُّونَ أَن تَشِيعَ ٱلۡفَٰحِشَةُ فِي ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

እነዚያ በእነዚያ ባመኑት ሰዎች ውስጥ መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነሱ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ አላህም ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም፡፡ {1} info

{1} ይህ አንቀጽና ቀጥሎ ያሉት ስለ ሙናፍቆች በሙእምኖች እናት ኣኢሻ ላይ የከፈቱት የውሸትና የስድብ ዘመቻ መልስ የተሰጠበት ነው። ዝርዝሩን በሀዲሱል ኢፍክ ውስጥ ያገኙታል።

التفاسير:

external-link copy
20 : 24

وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ وَأَنَّ ٱللَّهَ رَءُوفٞ رَّحِيمٞ

በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታውና እዝነቱ ባልነበረ አላህም ሩኅሩኅና አዛኝ ባልኾነ ኖሮ (ቶሎ ባጠፋችሁ ነበር)፡፡ info
التفاسير: