அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - முஹம்மத் சாதிக்

பக்க எண்:close

external-link copy
62 : 24

إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَإِذَا كَانُواْ مَعَهُۥ عَلَىٰٓ أَمۡرٖ جَامِعٖ لَّمۡ يَذۡهَبُواْ حَتَّىٰ يَسۡتَـٔۡذِنُوهُۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسۡتَـٔۡذِنُونَكَ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۚ فَإِذَا ٱسۡتَـٔۡذَنُوكَ لِبَعۡضِ شَأۡنِهِمۡ فَأۡذَن لِّمَن شِئۡتَ مِنۡهُمۡ وَٱسۡتَغۡفِرۡ لَهُمُ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

ምእመናን ማለት እነዚያ በአላህና በመልክተኛው ያመኑት፤ ከእርሱ ጋር በሚሰበሰብ ጉዳይ ላይ በኾኑ ጊዜ እስከሚያስፈቅዱ ድረስ የማይኼዱት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያ የሚያስፈቅዱህ እነርሱ እነዚያ በአላህና በመልክተኛው የሚያምኑት ናቸው፡፡ ለግል ጉዳያቸውም ፈቃድ በጠየቁህ ጊዜ ከእነሱ ለሻኸው ሰው ፍቀድለት፡፡ ለእነሱም አላህን ምሕረትን ለምንላቸው አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
63 : 24

لَّا تَجۡعَلُواْ دُعَآءَ ٱلرَّسُولِ بَيۡنَكُمۡ كَدُعَآءِ بَعۡضِكُم بَعۡضٗاۚ قَدۡ يَعۡلَمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ يَتَسَلَّلُونَ مِنكُمۡ لِوَاذٗاۚ فَلۡيَحۡذَرِ ٱلَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنۡ أَمۡرِهِۦٓ أَن تُصِيبَهُمۡ فِتۡنَةٌ أَوۡ يُصِيبَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ

በመካከላችሁ የመልክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደ መጥራት አታድርጉት፡፡ ከእናንተ ውስጥ እነዚያን እየተከለሉ በመስለክለክ የሚወጡትን አላህ በእርግጥ ያውቃቸዋል፡፡ እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
64 : 24

أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قَدۡ يَعۡلَمُ مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ وَيَوۡمَ يُرۡجَعُونَ إِلَيۡهِ فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُواْۗ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمُۢ

ንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ እናንተ በእርሱ ላይ ያላችሁበትን ኹኔታ በእርግጥ ያውቃል፡፡ ወደእርሱ የሚመለሱበትን ቀንም (ያውቃል) የሠሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير: