Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës

አል-አዕራፍ

external-link copy
1 : 7

الٓمٓصٓ

1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤ ሷድ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 7

كِتَٰبٌ أُنزِلَ إِلَيۡكَ فَلَا يَكُن فِي صَدۡرِكَ حَرَجٞ مِّنۡهُ لِتُنذِرَ بِهِۦ وَذِكۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِينَ

2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ልታስጠነቅቅበትና ለምእመናንም መገሰጫ እንዲሆን ወደ አንተ የተወረደ ቁርኣን ነው:: ስለዚህ ልብህ ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 7

ٱتَّبِعُواْ مَآ أُنزِلَ إِلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُمۡ وَلَا تَتَّبِعُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَۗ قَلِيلٗا مَّا تَذَكَّرُونَ

3. (ሰዎች ሆይ! ) ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደላችሁን መልዕክት ተከተሉ:: ከአላህ ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ:: ጥቂትን ብቻ ትገሰፃላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 7

وَكَم مِّن قَرۡيَةٍ أَهۡلَكۡنَٰهَا فَجَآءَهَا بَأۡسُنَا بَيَٰتًا أَوۡ هُمۡ قَآئِلُونَ

4. ከከተማ (ሰዎች) መካከል ልናጠፋቸው የፈለግነውንና ወዲያውኑ ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ህዝቦች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 7

فَمَا كَانَ دَعۡوَىٰهُمۡ إِذۡ جَآءَهُم بَأۡسُنَآ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

5. ቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ ጸሎታቸው «እኛ በደለኞች ነበርን።» ከማለት በስተቀር ሌላ አልነበረም:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 7

فَلَنَسۡـَٔلَنَّ ٱلَّذِينَ أُرۡسِلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَنَسۡـَٔلَنَّ ٱلۡمُرۡسَلِينَ

6. ከዚያ ወደ እነርሱ የተላከባቸውን ህዝቦችና መልዕክተኞቹንም እንጠይቃቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 7

فَلَنَقُصَّنَّ عَلَيۡهِم بِعِلۡمٖۖ وَمَا كُنَّا غَآئِبِينَ

7. ከዚያም በእነርሱ ላይ የነበሩትን ሁሉ ከእውቀት ጋር እንተርክላቸዋለን:: ከእነርሱ የራቅን አልነበርንምና:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 7

وَٱلۡوَزۡنُ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡحَقُّۚ فَمَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

8. የዚያን ቀኑ ሚዛን ትክክለኛ ነው:: እናም እነዚያ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸውም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ እነርሱ ብቻ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 7

وَمَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُم بِمَا كَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يَظۡلِمُونَ

9. እነዚያ ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸውም በአናቅጻችን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 7

وَلَقَدۡ مَكَّنَّٰكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَجَعَلۡنَا لَكُمۡ فِيهَا مَعَٰيِشَۗ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ

10. (ሰዎች ሆይ! ) በምድር ላይ በእርግጥም አስመቸናችሁ:: በእርሷም ላይ ለእናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ። ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 7

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَٰكُمۡ ثُمَّ صَوَّرۡنَٰكُمۡ ثُمَّ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ لَمۡ يَكُن مِّنَ ٱلسَّٰجِدِينَ

11. በእርግጥም ፈጠርናችሁ:: ከዚያም ቀረጽናችሁ:: ከዚያም ለመላዕክት « ለአደም ስገዱ።» አልን:: ወዲያዉም ሁሉም ሰገዱ:: ኢብሊስ ብቻ ሲቀር:: እሱማ ከሰጋጆቹ አልሆነም:: info
التفاسير: