Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës

አን ነጅም

external-link copy
1 : 53

وَٱلنَّجۡمِ إِذَا هَوَىٰ

1. በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 53

مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمۡ وَمَا غَوَىٰ

2. (እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ)፤ ባልደረባችሁ ሙሐመድ ከሐቅ አልተሳሳተም። አላፈነገጠም። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 53

وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلۡهَوَىٰٓ

3. ከልብ ወለድ ስሜቱም አይናገርም:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 53

إِنۡ هُوَ إِلَّا وَحۡيٞ يُوحَىٰ

4. እርሱ (ንግግሩ) ከአላህ የተወረደ እንጂ ሌላ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 53

عَلَّمَهُۥ شَدِيدُ ٱلۡقُوَىٰ

5. ሀይለ ብርቱ የሆነው አስተማረው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 53

ذُو مِرَّةٖ فَٱسۡتَوَىٰ

6. የእውቀት ባለቤት የሆነው:: ከዚያም ላይ ሆኖ ተመቻቸ። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 53

وَهُوَ بِٱلۡأُفُقِ ٱلۡأَعۡلَىٰ

7. በላይኛው አድማስ ላይ ሆኖ፤ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 53

ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ

8. ከዚያም (ነቢዩን) ቀረበው፤ በጣም ተጠጋውም። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 53

فَكَانَ قَابَ قَوۡسَيۡنِ أَوۡ أَدۡنَىٰ

9. ከዚያም የሁለት ደጋን ጫፎች ያህል ወይም ከዚያም ባነሰ ርቀት ላይ ሆነም:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 53

فَأَوۡحَىٰٓ إِلَىٰ عَبۡدِهِۦ مَآ أَوۡحَىٰ

10. እናም (አላህ) ለአገልጋዩ (ለሙሐመድ) ማውረድ የሻውን አወረደ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 53

مَا كَذَبَ ٱلۡفُؤَادُ مَا رَأَىٰٓ

11. ያየውን ነገር ሁሉ ልቦናው አላስተባበለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 53

أَفَتُمَٰرُونَهُۥ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ

12. ታዲያ (ከሓዲያን ሆይ!) በሚያየው ጉዳይ ላይ ትከራከሩታላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
13 : 53

وَلَقَدۡ رَءَاهُ نَزۡلَةً أُخۡرَىٰ

13. እርግጥ በሌላይቱም መውረድ (ነቢዩ ሙሐመድ መልዐኩ ጂብሪልን) አይቶታል:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 53

عِندَ سِدۡرَةِ ٱلۡمُنتَهَىٰ

14. ይኸዉም ሲድረቱ አል-ሙንተሃ (የመጨረሻቱ ቁርቁራ) በተባለው ዓለም ላይ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 53

عِندَهَا جَنَّةُ ٱلۡمَأۡوَىٰٓ

15. እርሷ ዘንድ መኖርያ የሆነችው ገነት አለች:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 53

إِذۡ يَغۡشَى ٱلسِّدۡرَةَ مَا يَغۡشَىٰ

16. (ቁርቁራይቱን) ሸፋኝ ነገር በሸፈናት ጊዜ (አየው)። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 53

مَا زَاغَ ٱلۡبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ

17. አይኑ አልተዘነበለም:: ወሰንም አላለፈም። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 53

لَقَدۡ رَأَىٰ مِنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِ ٱلۡكُبۡرَىٰٓ

18. ከጌታው ታላላቅ ተዐምራት በእርግጥ ተመለከተ። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 53

أَفَرَءَيۡتُمُ ٱللَّٰتَ وَٱلۡعُزَّىٰ

19. (ቁርይሾች ሆይ!) ላትንና ዑዛን አያችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
20 : 53

وَمَنَوٰةَ ٱلثَّالِثَةَ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ

20. ስለ ሶስተኛዋ መናትም የምታውቁትን እስቲ ንገሩኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 53

أَلَكُمُ ٱلذَّكَرُ وَلَهُ ٱلۡأُنثَىٰ

21. ለእናንተ ወንድ ወንድ ለእሱ ግን ሴት ሴት ታደርጋላችሁን:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 53

تِلۡكَ إِذٗا قِسۡمَةٞ ضِيزَىٰٓ

22. ይህ ተግባር አድሏዊ ክፍፍል ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 53

إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٞ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَمَا تَهۡوَى ٱلۡأَنفُسُۖ وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ ٱلۡهُدَىٰٓ

23. እነዚያ ጣዖታት እናንተና አባቶቻችሁ የሰየማችኋቸው ስሞች ብቻ እንጂ ሌላ አይደሉም::አላህ በእርሷ (መገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ጣኡት አምላኪዎች ሁሉ ከጌታቸው የተላከላቸው ቅኑ መመሪያ እያለ የሚከተሉት ግን ጥርጣሬንና ስሜትን ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 53

أَمۡ لِلۡإِنسَٰنِ مَا تَمَنَّىٰ

24. የሰው ልጅ የፈለገውን ሁሉ ያገኛልን? info
التفاسير:

external-link copy
25 : 53

فَلِلَّهِ ٱلۡأٓخِرَةُ وَٱلۡأُولَىٰ

25. መጪውን ዓለምም ሆነ የመጀመሪያው ዓለም የአላህ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 53

۞ وَكَم مِّن مَّلَكٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ

26. በሰማያት ውስጥ ካሉ መላዕክት አላህ የሚሻውንና የሚወደውን ለሰው ያማልዱ ዘንድ ከፈቀደላቸው በኋላ እንጂ ምልጃቸው የማይፈይድ አያሌዎች ናቸው:: info
التفاسير: