Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës

Numri i faqes:close

external-link copy
12 : 35

وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡبَحۡرَانِ هَٰذَا عَذۡبٞ فُرَاتٞ سَآئِغٞ شَرَابُهُۥ وَهَٰذَا مِلۡحٌ أُجَاجٞۖ وَمِن كُلّٖ تَأۡكُلُونَ لَحۡمٗا طَرِيّٗا وَتَسۡتَخۡرِجُونَ حِلۡيَةٗ تَلۡبَسُونَهَاۖ وَتَرَى ٱلۡفُلۡكَ فِيهِ مَوَاخِرَ لِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

12. ሁለቱ ባህሮች አይስተካከሉም ይህ ጣፋጭ፤ ጥምን ቆራጭ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው:: ይህኛው ደግሞ ጨው መርጋጋ ነው:: ከሁሉም እርጥብ ስጋን ትበላላችሁ:: የምትለብሷትንም ጌጥ ታወጣላችሁ። ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑትም መርከቦችን በእርሱ ውስጥ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 35

يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِي لِأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ لَهُ ٱلۡمُلۡكُۚ وَٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِيرٍ

13. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: ጸሀይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም እስከ ተወሰነለት ጊዜ ድረስ ይሮጣል :: ይህን የሚያደርገው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው :: ንግስናው የእሱ ብቻ ነው:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 35

إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا يَسۡمَعُواْ دُعَآءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُواْ مَا ٱسۡتَجَابُواْ لَكُمۡۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِيرٖ

14. ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም:: ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም:: በትንሳኤም ቀን እነርሱን በአላህ ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ አዋቂው አላህ ማንም አይነግርህም:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 35

۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ أَنتُمُ ٱلۡفُقَرَآءُ إِلَى ٱللَّهِۖ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ

15. እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ:: አላህም እርሱ ተብቃቂውና ምስጉኑ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 35

إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَأۡتِ بِخَلۡقٖ جَدِيدٖ

16. (አላህ) ቢሻ ያስወግዳችሁና አዲስን ፍጡር ያመጣል (ይፈጥራል):: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 35

وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٖ

17. ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 35

وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ وَإِن تَدۡعُ مُثۡقَلَةٌ إِلَىٰ حِمۡلِهَا لَا يُحۡمَلۡ مِنۡهُ شَيۡءٞ وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰٓۗ إِنَّمَا تُنذِرُ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَۚ وَمَن تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفۡسِهِۦۚ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلۡمَصِيرُ

18. ኃጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላውን ሸክም አትሸከምም:: የራሷ ወንጀል የከበዳትም ነፍስ እርዳታ እንዲደረግላት ብትጠራ ተጠሪው የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን ከእርሷ አንድን ነገር የሚሸከምላት አታገኝም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን፤ በሩቅ የሚፈሩትን ሶላትንም አስተካክለው የሚሰገዱትን ብቻ ነው:: ከወንጀልም የተጥራራ ሁሉ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው:: መመለሻዉም ወደ አላህ ብቻ ነው:: info
التفاسير: