Përkthimi i kuptimeve të Kuranit Fisnik - Përkthimi emherisht - Akademia e Afrikës

Numri i faqes:close

external-link copy
16 : 3

ٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَآ إِنَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَا وَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ

16. (እነርሱም) እነዚያ «ጌታችን ሆይ! እኛ ባንተ አመንን። ኃጢአቶቻችንን ማርልን። የእሳትን ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 3

ٱلصَّٰبِرِينَ وَٱلصَّٰدِقِينَ وَٱلۡقَٰنِتِينَ وَٱلۡمُنفِقِينَ وَٱلۡمُسۡتَغۡفِرِينَ بِٱلۡأَسۡحَارِ

17. እነርሱም ታጋሾች፤ እውነተኞች፤ ታዛዦች፤ ለጋሾችና በሌሊት መጨረሻዎች ሰዓታት ላይ አላህን ምህረት የሚለምኑ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 3

شَهِدَ ٱللَّهُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَأُوْلُواْ ٱلۡعِلۡمِ قَآئِمَۢا بِٱلۡقِسۡطِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

18. አላህ (በማስተካከል) ቀጥ ያለ ሲሆን ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የሌለ መሆኑን መሰከረ። መላዕክትና የእውቀት ባለቤቶችም መሰከሩ። ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም:: እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነው። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 3

إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلۡإِسۡلَٰمُۗ وَمَا ٱخۡتَلَفَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُ بَغۡيَۢا بَيۡنَهُمۡۗ وَمَن يَكۡفُرۡ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ

19. አላህ ዘንድ የተወደደው ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነው:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎች በመካከላቸው ባለው ምቀኝነት እውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም:: በአላህ አናቅጽ ለሚክድ ሁሉ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 3

فَإِنۡ حَآجُّوكَ فَقُلۡ أَسۡلَمۡتُ وَجۡهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ ٱتَّبَعَنِۗ وَقُل لِّلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡأُمِّيِّـۧنَ ءَأَسۡلَمۡتُمۡۚ فَإِنۡ أَسۡلَمُواْ فَقَدِ ٱهۡتَدَواْۖ وَّإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا عَلَيۡكَ ٱلۡبَلَٰغُۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِٱلۡعِبَادِ

20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም «ፊቴን ለአላህ ብቻ ሰጠሁ። የተከተሉኝም እንደዚሁ ለአላህ ብቻ ሰጡ።» በላቸው:: ለእነዚያም መጽሐፉን ለተሰጡ ሰዎችና ለመሃይማኑ (ዐረቦች)፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው:: ቢሰልሙም በእርግጥ ወደቀናው መንገድ ተመሩ:: እምቢ ቢሉ ግን ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትን ማድረስ ብቻ ነው:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 3

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقۡتُلُونَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ بِغَيۡرِ حَقّٖ وَيَقۡتُلُونَ ٱلَّذِينَ يَأۡمُرُونَ بِٱلۡقِسۡطِ مِنَ ٱلنَّاسِ فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ አናቅጽ የሚክዱ፤ ነብያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ፤ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኛነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 3

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

22. እነዚያ በቅርቢቱም ሆን በመጨረሻይቱ ዓለም ስራዎቻቸው የተበላሹ ናቸው:: ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም:: info
التفاسير: