Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

Número de página:close

external-link copy
75 : 23

۞ وَلَوۡ رَحِمۡنَٰهُمۡ وَكَشَفۡنَا مَا بِهِم مِّن ضُرّٖ لَّلَجُّواْ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ

75. ባዘንላቸውና በእነርሱ ያለውን ጉዳትም ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋዥቁ ሆነው ይዘወትሩ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 23

وَلَقَدۡ أَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ فَمَا ٱسۡتَكَانُواْ لِرَبِّهِمۡ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ

76. በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው:: ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም:: የሚዋደቁም አይደሉም። info
التفاسير:

external-link copy
77 : 23

حَتَّىٰٓ إِذَا فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابٗا ذَا عَذَابٖ شَدِيدٍ إِذَا هُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ

77. በእነርሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የሆነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
78 : 23

وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ

78. እርሱም ያ መስሚያዎችን፤ ማያዎችንና ልቦችን ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው:: ጥቂትን እንጂ አታመሰግኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
79 : 23

وَهُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ

79. እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው:: በመጨረሻም ጊዜ ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
80 : 23

وَهُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَلَهُ ٱخۡتِلَٰفُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

80. እርሱም ያ ህያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው:: የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው :: አታውቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
81 : 23

بَلۡ قَالُواْ مِثۡلَ مَا قَالَ ٱلۡأَوَّلُونَ

81. ይልቁንም የመካ ከሓዲያን ልክ የፊተኞቹ ህዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
82 : 23

قَالُوٓاْ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ

82. አሉም: «በሞትንና አፈርና አጥንቶች በሆንን ጊዜ እኛ እንደገና ተቀስቃሾች ነን? info
التفاسير:

external-link copy
83 : 23

لَقَدۡ وُعِدۡنَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا هَٰذَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

83. «ይህንን ሁኔታ እኛም ሆነ ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
84 : 23

قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ እስቲ ንገሩኝ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
85 : 23

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

85. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ የአላህ ነው።» ይሉሃል። «ታዲያ አትገሠጹምን?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
86 : 23

قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ

86. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰባቱ ሰማያት ጌታ የታላቁም ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
87 : 23

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ

87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
88 : 23

قُلۡ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

88. «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ፤ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ ከሆናችሁ (እስቲ መልሱልኝ)» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
89 : 23

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ

89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል፤ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው። info
التفاسير: