Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

Número de página:close

external-link copy
18 : 23

وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٖ فَأَسۡكَنَّٰهُ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَإِنَّا عَلَىٰ ذَهَابِۭ بِهِۦ لَقَٰدِرُونَ

18. ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን:: በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው:: እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 23

فَأَنشَأۡنَا لَكُم بِهِۦ جَنَّٰتٖ مِّن نَّخِيلٖ وَأَعۡنَٰبٖ لَّكُمۡ فِيهَا فَوَٰكِهُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ

19. በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች አትክልቶችን ለእናንተ አስገኘንላችሁ:: በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 23

وَشَجَرَةٗ تَخۡرُجُ مِن طُورِ سَيۡنَآءَ تَنۢبُتُ بِٱلدُّهۡنِ وَصِبۡغٖ لِّلۡأٓكِلِينَ

20. ከሲና ተራራም የምትወጣ ዛፍ በቅባትና ለበይዎች መባያ በሚሆን ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅልን አስገኘንላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 23

وَإِنَّ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَنۡعَٰمِ لَعِبۡرَةٗۖ نُّسۡقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهَا وَلَكُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ كَثِيرَةٞ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ

21. (ሰዎች ሆይ!) እናንተም በግመል፤ በከብት በፍየልና በበግ መገምገሚያ አላችሁ:: በሆዶችዋ ውስጥ ካለው ወተት እናጠጣችኋለን:: ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ:: ከእርሷም ትበላላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 23

وَعَلَيۡهَا وَعَلَى ٱلۡفُلۡكِ تُحۡمَلُونَ

22. በእርሷም ላይና በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 23

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ

23. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ በእርግጥ ላክነው። ወዲያዉም «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 23

فَقَالَ ٱلۡمَلَؤُاْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُرِيدُ أَن يَتَفَضَّلَ عَلَيۡكُمۡ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَنزَلَ مَلَٰٓئِكَةٗ مَّا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِيٓ ءَابَآئِنَا ٱلۡأَوَّلِينَ

24. ከህዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል። አላህም ቢፈልግ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር። ይህንንም የሚለውን በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 23

إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلُۢ بِهِۦ جِنَّةٞ فَتَرَبَّصُواْ بِهِۦ حَتَّىٰ حِينٖ

25. «እርሱ እብደት ያለበት ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: በእርሱም እስከ ጊዜው ድረስ ተጠባበቁ።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 23

قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ

26. ኑሕም «ጌታዬ ሆይ! ስለ አስተባበሉኝ እርዳኝ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 23

فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ أَنِ ٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا فَإِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ فَٱسۡلُكۡ فِيهَا مِن كُلّٖ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ مِنۡهُمۡۖ وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ

27. ወደ እርሱ እንዲህ ስንል ላክን: «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችን ታንኳን ስራ። ከዚያ ትእዛዛችን በመጣና ምድጃው (እቶኑ) በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ነገር ሁለት ሁለት ዓይነቶችንና ቤተሰቦችህን ከእነርሱ መካከል ጠፊ በመሆኑ ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር አስገባ። በእነዚያ ራሳቸውን በአላህ በመካድ በበደሉት ሰዎች ጉዳይ አታነጋግረኝ። እነርሱ በውኃ ተሰማጪዎች ናቸውና። info
التفاسير: