Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie

Pagina nummer:close

external-link copy
62 : 9

يَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ لَكُمۡ لِيُرۡضُوكُمۡ وَٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ أَحَقُّ أَن يُرۡضُوهُ إِن كَانُواْ مُؤۡمِنِينَ

62. አላህንና መልዕክተኛውን ሊያስወድዱ ሲገባቸው እናንተን ሊያስወድዷችሁ ዘንድ በአላህ ይምሉላችኋል። ትክክለኛ አማኞች ከሆኑ (ግን አላህንና መልዕክተኛው ሊያስወድዱ ይገባቸዋል):: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 9

أَلَمۡ يَعۡلَمُوٓاْ أَنَّهُۥ مَن يُحَادِدِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَأَنَّ لَهُۥ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدٗا فِيهَاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡخِزۡيُ ٱلۡعَظِيمُ

63. አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከር ሰው ሁሉ በውስጡ ዘውታሪ ሲሆን የተዘጋጀችለት የገሀነም እሳት መሆኑን አያውቁምን? ይህ ደግሞ ታላቅ ውርደት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 9

يَحۡذَرُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيۡهِمۡ سُورَةٞ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمۡۚ قُلِ ٱسۡتَهۡزِءُوٓاْ إِنَّ ٱللَّهَ مُخۡرِجٞ مَّا تَحۡذَرُونَ

64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ የሚነግራቸው ምዕራፍ በእነርሱ ላይ መወረዱን ዘወትር ይፈራሉ:: «ተሳለቁ:: አላህ የምትፈሩትን ነገር ሁሉ ገላጭ ነው።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 9

وَلَئِن سَأَلۡتَهُمۡ لَيَقُولُنَّ إِنَّمَا كُنَّا نَخُوضُ وَنَلۡعَبُۚ قُلۡ أَبِٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ وَرَسُولِهِۦ كُنتُمۡ تَسۡتَهۡزِءُونَ

65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትጠይቃቸው «እኛ የምንዘባርቅና የምንጫወት ሰዎች ብቻ ነበርን።» ይላሉ:: «በአላህ፤ በአናቅጹና በመልዕክተኛው ላይ ትቀልዱ ነበራችሁን?» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 9

لَا تَعۡتَذِرُواْ قَدۡ كَفَرۡتُم بَعۡدَ إِيمَٰنِكُمۡۚ إِن نَّعۡفُ عَن طَآئِفَةٖ مِّنكُمۡ نُعَذِّبۡ طَآئِفَةَۢ بِأَنَّهُمۡ كَانُواْ مُجۡرِمِينَ

66. (አስመሳዮች ሆይ!) አታመካኙ ከእምነታችሁ በኋላ በእርግጥ ክዳችኋልና:: ከናንተ አንዷን ቡድን ብንምር የሌላዋን ቡድን አባላት ግን ኃጢአተኞች በመሆናቸው እንቀጣለን:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 9

ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتُ بَعۡضُهُم مِّنۢ بَعۡضٖۚ يَأۡمُرُونَ بِٱلۡمُنكَرِ وَيَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَقۡبِضُونَ أَيۡدِيَهُمۡۚ نَسُواْ ٱللَّهَ فَنَسِيَهُمۡۚ إِنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ

67. የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው:: በመጥፎ ነገር ያዛሉ:: ከደግ ነገርም ይከለክላሉ:: እጆቻቸውን ከልግስና ይሰበስባሉ:: ለአላህ መታዘዝን ረሱ (ተዉ):: ስለዚህ እርሱም ተዋቸው:: አስመሳዮቹ አመጸኞች ማለት እነርሱው ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 9

وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلۡكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ هِيَ حَسۡبُهُمۡۚ وَلَعَنَهُمُ ٱللَّهُۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ مُّقِيمٞ

68. የወንድ አስመሳዮችንና የሴት አስመሳዮችን እንዲሁም ከሓዲያንን የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ ቃል ገብቶላቸዋል:: እርሷ በቂያቸው ናት:: አላህ ረግሟቸዋል:: ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير: