Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie

አል ኢንሺቃቅ

external-link copy
1 : 84

إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنشَقَّتۡ

1. ሰማይ በተቀደደች (በተሰነጠቀች) ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 84

وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ

2. የጌታዋንም ትዕዛዝ በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 84

وَإِذَا ٱلۡأَرۡضُ مُدَّتۡ

3. ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 84

وَأَلۡقَتۡ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتۡ

4. በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በሆነች ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 84

وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ

5. ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (ልትስማ) ተገባትም፤ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 84

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدۡحٗا فَمُلَٰقِيهِ

6. አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን በሞት እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ። ተገናኚዉም ነህ። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 84

فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ

7. ያ! መጽሐፉን በቀኝ እጅ የተሰጠውማ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 84

فَسَوۡفَ يُحَاسَبُ حِسَابٗا يَسِيرٗا

8. በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 84

وَيَنقَلِبُ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورٗا

9. ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ሆኖ (በደስታ) ይመለሳል:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 84

وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ وَرَآءَ ظَهۡرِهِۦ

10. ያ ! መጽሐፉን በጀርባው በኩል የተሰጠው ግን info
التفاسير:

external-link copy
11 : 84

فَسَوۡفَ يَدۡعُواْ ثُبُورٗا

11. (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 84

وَيَصۡلَىٰ سَعِيرًا

12. የተጋጋመች እሳትንም ይገባል:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 84

إِنَّهُۥ كَانَ فِيٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورًا

13. እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፤ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 84

إِنَّهُۥ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ

14. እርሱም ወደ አላህ እንደማይመለስ አሰበ። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 84

بَلَىٰٓۚ إِنَّ رَبَّهُۥ كَانَ بِهِۦ بَصِيرٗا

15. አይደለም (ይመለሳል)፤ ጌታው በእርሱ (መመለስ) አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 84

فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلشَّفَقِ

16. ስለሆነም በወጋገኑ እምላለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 84

وَٱلَّيۡلِ وَمَا وَسَقَ

17. በሌሊቱና በሰበሰበዉም ሁሉ፤ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 84

وَٱلۡقَمَرِ إِذَا ٱتَّسَقَ

18. በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 84

لَتَرۡكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٖ

19. ከአንድ እርከን ወደ ሌላ እርከን ትሸጋገራላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 84

فَمَا لَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

20. የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው ( ምን ሆነው ነው)? info
التفاسير:

external-link copy
21 : 84

وَإِذَا قُرِئَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقُرۡءَانُ لَا يَسۡجُدُونَۤ۩

21. በእነርሱ ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱትስ ለእነርሱ ምን አላቸውና ነው? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 84

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُكَذِّبُونَ

22. በእርግጥ እነዚያ የካዱት ያስተባብላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 84

وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُوعُونَ

23. አላህ በልቦቻቸው የሚቋጥሩትን ሁሉ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 84

فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 84

إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونِۭ

25.እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ተግባራትን የሰሩት ሲቀሩ፤ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው። info
التفاسير: