Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie

Pagina nummer:close

external-link copy
12 : 7

قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسۡجُدَ إِذۡ أَمَرۡتُكَۖ قَالَ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡهُ خَلَقۡتَنِي مِن نَّارٖ وَخَلَقۡتَهُۥ مِن طِينٖ

12. አላህም «ዲያብሎስ ሆይ! ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው:: ዲያብሎስም «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ:: እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 7

قَالَ فَٱهۡبِطۡ مِنۡهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَٱخۡرُجۡ إِنَّكَ مِنَ ٱلصَّٰغِرِينَ

13. (አላህም) «ከእርሷ ውረድ:: በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና:: ውጣም:: አንተ ከወራዶቹ ነህና።» አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 7

قَالَ أَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ

14. (ኢብሊስም): «እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 7

قَالَ إِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ

15. አላህ «አንተ ከሚቆዩት ነህ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 7

قَالَ فَبِمَآ أَغۡوَيۡتَنِي لَأَقۡعُدَنَّ لَهُمۡ صِرَٰطَكَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ

16. (ኢብሊስም) አለ: «ስላጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 7

ثُمَّ لَأٓتِيَنَّهُم مِّنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ وَعَنۡ أَيۡمَٰنِهِمۡ وَعَن شَمَآئِلِهِمۡۖ وَلَا تَجِدُ أَكۡثَرَهُمۡ شَٰكِرِينَ

17. «ከዚያም ከበስተፊቶቻቸው፤ ከየኋላቸዉም፤ ከየቀኞቻቸውና ከየግራዎቻቸዉም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ:: አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ሆነው አታገኛቸዉም።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 7

قَالَ ٱخۡرُجۡ مِنۡهَا مَذۡءُومٗا مَّدۡحُورٗاۖ لَّمَن تَبِعَكَ مِنۡهُمۡ لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمۡ أَجۡمَعِينَ

18. «የተጠላህ ብራሪ ስትሆን ከእርሷ ውጣ:: ከእነርሱ መካከልም አንተን ከተከተሉህ እና አንተንም ሁላችሁንም ገሀነምን በእርግጥ በእናንተ እሞላታለሁ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 7

وَيَٰٓـَٔادَمُ ٱسۡكُنۡ أَنتَ وَزَوۡجُكَ ٱلۡجَنَّةَ فَكُلَا مِنۡ حَيۡثُ شِئۡتُمَا وَلَا تَقۡرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

19. ‹‹አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ እንደፈለጋችሁ ተመገቡ:: ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ:: ራሳቸውን ከሚበድሉት ትሆናላችሁና።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 7

فَوَسۡوَسَ لَهُمَا ٱلشَّيۡطَٰنُ لِيُبۡدِيَ لَهُمَا مَا وُۥرِيَ عَنۡهُمَا مِن سَوۡءَٰتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَىٰكُمَا رَبُّكُمَا عَنۡ هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةِ إِلَّآ أَن تَكُونَا مَلَكَيۡنِ أَوۡ تَكُونَا مِنَ ٱلۡخَٰلِدِينَ

20. ሰይጣንም ከሀፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው። «ጌታችሁ እኮ መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ከዘላለም ኗዋሪዎቹ እንዳትሆኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 7

وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ

21. «እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሯችሁ ነኝ።» ሲልም ማለላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 7

فَدَلَّىٰهُمَا بِغُرُورٖۚ فَلَمَّا ذَاقَا ٱلشَّجَرَةَ بَدَتۡ لَهُمَا سَوۡءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخۡصِفَانِ عَلَيۡهِمَا مِن وَرَقِ ٱلۡجَنَّةِۖ وَنَادَىٰهُمَا رَبُّهُمَآ أَلَمۡ أَنۡهَكُمَا عَن تِلۡكُمَا ٱلشَّجَرَةِ وَأَقُل لَّكُمَآ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ لَكُمَا عَدُوّٞ مُّبِينٞ

22. በማታለልም አዋረዳቸው:: ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ሀፍረተ ገላቸው የሁለቱም ተገለጠባቸው:: ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ (ይለጥፉ) ጀመር:: ጌታቸዉም «ይህችን ዛፍ አልከለከልኳችሁም ነበርን? ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁም ነበርን?» ሲል ጠራቸው። info
التفاسير: