Vertaling van de betekenissen Edele Qur'an - De Amhaarse vertaling - Afrika Academie

Pagina nummer:close

external-link copy
10 : 3

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَن تُغۡنِيَ عَنۡهُمۡ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيۡـٔٗاۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمۡ وَقُودُ ٱلنَّارِ

10. እነዚያ የካዱትን ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) አያስጥሏቸዉም። እነዚያም እነርሱ የእሳት ማገዶዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 3

كَدَأۡبِ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡۗ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ

11. ምሳሊያቸው ልክ እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደነዚያ ከበፊታቸዉም እንደነበሩት ሕዝቦች ልማድ ነው:: በአናቅጻችን አስተባበሉ:: እናም አላህ በኃጢአቶቻቸው ቀጣቸው:: አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 3

قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ سَتُغۡلَبُونَ وَتُحۡشَرُونَ إِلَىٰ جَهَنَّمَۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ

12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ በአላህ ለካዱ ሰዎች «በቅርብ ጊዜ ትሸነፋላችሁ:: ከዚያም በገሀነም ትሰበሰባላችሁ:: ምንጣፊቱም (ገሀነም) ምን ትከፋ!» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 3

قَدۡ كَانَ لَكُمۡ ءَايَةٞ فِي فِئَتَيۡنِ ٱلۡتَقَتَاۖ فِئَةٞ تُقَٰتِلُ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَأُخۡرَىٰ كَافِرَةٞ يَرَوۡنَهُم مِّثۡلَيۡهِمۡ رَأۡيَ ٱلۡعَيۡنِۚ وَٱللَّهُ يُؤَيِّدُ بِنَصۡرِهِۦ مَن يَشَآءُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبۡرَةٗ لِّأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ

13. በእነዚያ (የበድር) ቀን በተጋጠሙት ሁለት ቡድኖች ለእናንተ ብዙ ተዓምራት አሉ:: አንደኛዋ ቡድን በአላህ መንገድ ትጋደላለች:: ሌላይቱ ቡድን ደግሞ ከሓዲ ናት። በዓይን አስተያየት እጥፋቸው ሆነው ያዩዋቸዋል (በቁጥር የነርሱ እጥፍ ሁነው በአይናቸው ተመለከቷቸው)። አላህ በእርዳታው የሚሻውን ሁሉ ያበረታልና። በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች ሁሉ በእርግጥ መገሰጫ አለበት:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 3

زُيِّنَ لِلنَّاسِ حُبُّ ٱلشَّهَوَٰتِ مِنَ ٱلنِّسَآءِ وَٱلۡبَنِينَ وَٱلۡقَنَٰطِيرِ ٱلۡمُقَنطَرَةِ مِنَ ٱلذَّهَبِ وَٱلۡفِضَّةِ وَٱلۡخَيۡلِ ٱلۡمُسَوَّمَةِ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ وَٱلۡحَرۡثِۗ ذَٰلِكَ مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسۡنُ ٱلۡمَـَٔابِ

14. ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆች፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከተከማቹ ገንዘቦች፣ ከተሰማሩ ፈረሶች፣ ከግመል ከከብትና ከፍየል፣ ከአዝመራም የሆኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመላቸው (ሰዎች ዘንድ የተወደዱ ተደረገላቸው)። ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቃቀሚያ ብቻ ነው:: አላህ ግን እርሱ ዘንድ መልካም የሆነ መመለሻ (ገነት) አለው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 3

۞ قُلۡ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيۡرٖ مِّن ذَٰلِكُمۡۖ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ عِندَ رَبِّهِمۡ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَأَزۡوَٰجٞ مُّطَهَّرَةٞ وَرِضۡوَٰنٞ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِٱلۡعِبَادِ

15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከዚህ ከተዋበላችሁ ጉዳይ የሚበልጥን ልንገራችሁን? እርሱም ለእነዚያ አላህን ለሚፈሩ ሁሉ በጌታቸው ዘንድ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲሆኑ ንጹህ ሚስቶችና ከአላህ የሆነ ውዴታም አለላቸው:: አላህም ባርያዎቹን ተመልካች ነው።» በላቸው። info
التفاسير: